የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 25, 2013 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
1. ኢየሱስ “የሚያዝኑ ደስተኞች” እንደሚሆኑ የተናገረው ለምንድን ነው? (ማቴ. 5:4) [ጥር 7, w09 2/15 ገጽ 6 አን. 6]
2. ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ባስተማረው የጸሎት ናሙና ላይ “ወደ ፈተና አታግባን” ሲል ምን ማለቱ ነው? (ማቴ. 6:13) [ጥር 7, w04 2/1 ገጽ 16 አን. 13]
3. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ “የሰው ልጅ እስከሚመጣ ድረስ” የስብከት ክልላቸውን እንደማያዳርሱ የተናገረው ለምንድን ነው? (ማቴ. 10:23) [ጥር 14, w10 9/15 ገጽ 9 አን. 12፤ gt ገጽ 170 አን. 1]
4. ኢየሱስ ስለ ሰናፍጩ ዘር የተናገረው ምሳሌ ጎላ አድርጎ የሚገልጻቸው ሁለት ነገሮች ምንድን ናቸው? (ማቴ. 13:31, 32) [ጥር 21, w08 7/15 ገጽ 17-18 አን. 3-8]
5. ኢየሱስ “ካልተመለሳችሁና እንደ ልጆች ካልሆናችሁ በምንም ዓይነት ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም” ሲል ምን ትምህርት እያስተላለፈ ነበር? (ማቴ. 18:3) [ጥር 28, w07 2/1 ገጽ 9-10 አን. 2-3]
6. ኢየሱስ “አንተው ራስህ ተናገርከው” ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ማቴ. 26:63, 64) [የካ. 11, w11 6/1 ገጽ 18]
7. ኢየሱስ “የሰንበትም እንኳ ጌታ” የተባለው ለምንድን ነው? (ማር. 2:28) [የካ. 18, w08 2/15 ገጽ 28 አን. 7]
8. ኢየሱስ ስለ እናቱና ስለ ወንድሞቹ የተናገረው ሐሳብ ምን ትርጉም አለው? እኛንስ ምን ያስተምረናል? (ማር. 3:31-35) [የካ. 18, w08 2/15 ገጽ 29 አን. 5]
9. በማርቆስ 8:22-25 ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ኢየሱስ ዓይነ ስውሩን ሰው ደረጃ በደረጃ የፈወሰው ለምንድን ነው? ከዚህስ ምን ትምህርት እናገኛለን? [የካ. 25, w00 2/15 ገጽ 17 አን. 7]
10. በማርቆስ 8:32-34 ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው ኢየሱስ ጴጥሮስ ሲገሥጸው ምላሽ ከሰጠበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን? [የካ. 25, w08 2/15 ገጽ 29 አን. 6]