የካቲት 25 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
የካቲት 25 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 6 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 2 ከአን. 1-8 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ማርቆስ 5-8 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
5 ደቂቃ፦ “ማቋረጥ አለባችሁ?” በውይይት የሚቀርብ።
10 ደቂቃ፦ ልናውጀው የሚገባ መልእክት—‘ስለ ኢየሱስ መመሥከር።’ የአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ገጽ 275 ላይ ከሚገኘው ንዑስ ርዕስ አንስቶ እስከ ገጽ 278 መጨረሻ ድረስ ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በግለት የሚቀርብ ንግግር።
15 ደቂቃ፦ ይሖዋ እንድንሰብክ ኃይል ይሰጠናል። (ፊልጵ. 4:13) የጤና ችግር ቢኖርባቸውም በስብከቱ ሥራ በቅንዓት ለሚካፈሉ ሁለት ወይም ሦስት አስፋፊዎች ቃለ ምልልስ አድርግ። ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች አጋጥመዋቸዋል? በተስፋ መቁረጥ ስሜት እንዳይዋጡ የረዳቸው ምንድን ነው? የጉባኤው አባላት እርዳታ ያበረከቱላቸው በየትኞቹ ተግባራዊ መንገዶች ነው? በአገልግሎት አዘውትረው በመካፈላቸው ምን ጥቅም አግኝተዋል?
መዝሙር 42 እና ጸሎት