መዝሙር 42
‘ደካማ የሆኑትን እርዱ’
በወረቀት የሚታተመው
1. ብዙ ነው ድክመታችን፣
የሁላችንም።
አምላክ ግን ይወደናል፤
ያስብልናል።
እሱ መሐሪ ነው፤
ፍቅሩ ወደር የለው።
እኛም ለተጨነቁት
አዛኝ እንሁን።
2. ድክመቱን የሚያስተውል፣
ለሌሎች ያዝናል።
ሕይወት ማግኘት የቻልነው፣
በ’የሱስ ደም ነው።
አምላክ ያበረታል፤
ደካማን አይረሳም።
ይሰማን ጭንቀታቸው፤
እናጽናናቸው።
3. ደካሞችን ከመንቀፍ
እናግዛቸው።
ደግነት በማሳየት
እናበርታቸው።
ሳንሰለች በመርዳት፣
ብንሆናቸው ብርታት፣
ደስተኛ ይሆናሉ፤
እፎይ ይላሉ።
(በተጨማሪም ኢሳ. 35:3, 4ን፣ 2 ቆሮ. 11:29ን እና ገላ. 6:2ን ተመልከት።)