ማስታወቂያዎች
◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች፦ መጋቢት እና ሚያዝያ፦ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች። ተመላልሶ መጠየቅ ስታደርጉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አሊያም ደግሞ የግለሰቡን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ ከተባሉት ብሮሹሮች መካከል አንዱን በማበርከት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። ግንቦት እና ሰኔ፦ ከሚከተሉት ትራክቶች አንዱን ማበርከት ትችላላችሁ፦ በቤተሰብ ኑሮ ተደሰት፣ ዓለምን የሚገዛው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን ማመን የሚችሉት ለምንድን ነው? ወይም እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ? ግለሰቡ ፍላጎት ካለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ አሊያም አምላክን ስማ ወይም አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ በተባለው ብሮሹር ተጠቅማችሁ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንደሚችል ልታሳዩት ትችላላችሁ።
◼ የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው ማክሰኞ፣ መጋቢት 26 ቀን 2013 (እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር መጋቢት 17 ቀን 2005) ነው። ጉባኤያችሁ ማክሰኞ ዕለት ስብሰባ የሚያደርግ ከሆነ ይህን ስብሰባ የመንግሥት አዳራሹ ነፃ ወደሚሆንበት ሌላ ቀን ማዛወር ይኖርባችኋል። በዚያ ሳምንት የአገልግሎት ስብሰባ ሳይቀርብ ከቀረ ለጉባኤያችሁ አስፈላጊ የሆኑት ክፍሎች በዚያው ወር ባለ የአገልግሎት ስብሰባ ላይ እንዲካተቱ የሽማግሌዎች አካል አስተባባሪው ፕሮግራሞቹ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ይችላል። የወረዳ የበላይ ተመልካች ጉባኤያችሁን የሚጎበኝ ከሆነ ማክሰኞ ማታ የሚደረገውን ስብሰባ በሳምንቱ ውስጥ በሌላ ቀን ማድረግ ይኖርባችኋል።