የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በጥቅምት ወር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ አገር ቋንቋ ትምህርት ቤት የተዘጋጀ ሲሆን በቻይንኛ ቋንቋ ማገልገል የሚፈልጉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ከ30 የሚበልጡ አስፋፊዎችና አቅኚዎች በዚህ ትምህርት ቤት መካፈል ጀምረዋል። ሥልጠናው ሦስት ወር ይወስዳል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተማሪዎቹ ሰላምታ የመስጠት፣ አጭር መግቢያ የመጠቀምና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን የመምራት ችሎታቸው ደረጃ በደረጃ እንዲያድግ በክፍል ውስጥና በመስክ ላይ ሥልጠና ያገኛሉ። በቅርብ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በኢትዮጵያ ውስጥ የተማረች የመጀመሪያዋ ቻይናዊ እህት ተጠምቃለች። እዚህ የሚሠሩ በርካታ የሩቅ ምሥራቅ ተወላጆች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፍላጎት እያሳዩ ነው። ሁሉም የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንዲያገኙ ምኞታችን ነው።