ጥቅምት 21 የሚጀምር ሳምንት
ጥቅምት 21 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መዝሙር 33 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
cf ምዕ. 13 ከአን. 9-17 (30 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ተሰሎንቄ 1-5 እስከ 2 ተሰሎንቄ 1-3 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ 1 ተሰሎንቄ 2:9-20 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ ሰለሞን ካደረጋቸው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገሮች ምን ትምህርት እናገኛለን?—ሮም 15:4 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖቶችን ስለ መቀላቀል ምን አመለካከት አለው?—rs ገጽ 324 አን. 1 እስከ ገጽ 325 አን. 1 (5 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ማርቆስ 1:40-42፤ ማርቆስ 7:32-35 እና ሉቃስ 8:43-48 እንዲነበቡ አድርግ። ከዚያም እነዚህ ዘገባዎች ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅሙን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።
15 ደቂቃ፦ “ልጆቻችሁን ለማስተማር ድረ ገጻችንን ተጠቀሙ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። አንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ “ለወላጆች የተሰጠ መመሪያ” የሚለው የት እንደሚገኝ ተናገር፤ እንዲሁም እዚያ ላይ ከቀረቡት መመሪያዎች መካከል አንዱን እንደ ምሳሌ ጥቀስ። አንቀጽ 4 ላይ ስትወያዩ ደግሞ ቤተሰቦች፣ የቤተሰብ አምልኮ ሲያደርጉ ሕጋዊ ድረ ገጻችንን በጥሩ ሁኔታ እንዴት እንደተጠቀሙበት እንዲናገሩ ጋብዝ።
መዝሙር 41 እና ጸሎት