የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
ያለፈው የአገልግሎት ዓመት 9,649 የደረሰ ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር እንዲሁም 2.3 በመቶ ዓመታዊ እድገት በማስመዝገብ ተጠናቅቋል። በተጨማሪም 498 ሰዎች ተጠምቀዋል። የዘወትር አቅኚዎች ቁጥርም ቢሆን 12 በመቶ ጭማሪ የነበረው ሲሆን በመስከረም ወር 181 ተጨማሪ የዘወትር አቅኚዎች ተገኝተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሃያ ሁለት የሚሆኑ አስፋፊዎች ማንበብና መጻፍ ተምረዋል፤ ይህ በእርግጥም የሚያስመሰግን ሥራ ነው። ብሮሹሮችን በማበርከት ረገድ 42 በመቶ እድገት የታየ ሲሆን መጽሔቶችን በማበርከት ረገድ ደግሞ 11 በመቶ ጭማሪ ተገኝቷል። ይህም ብዙ ተመላልሶ መጠየቆችን እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማግኘት በር እንደሚከፍት ተስፋ እናደርጋለን።