መስከረም 15 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
መስከረም 15 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 15 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 7 ከአን. 9-13 እና በገጽ 56 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘኍልቍ 26-29 (10 ደቂቃ)
ቁ. 1፦ ዘኍልቍ 27:15 እስከ 28:10 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ቁ. 2፦ አምላክ፣ ዲያብሎስ አድርጎ የፈጠረው አካል የለም—rs ገጽ 362 አን. 2 (5 ደቂቃ)
ቁ. 3፦ አዳም—ኃጢአት ያስከተለው ክፉ መዘዝ—w10 5/1 ገጽ 4-6 (5 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
15 ደቂቃ፦ ምን አከናውነናል? በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ የሚቀርብ ንግግር። በነሐሴ ወር የተካሄደውን ልዩ ዘመቻ ጨምሮ ጉባኤው ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ያደረገውን እንቅስቃሴ ከልስ። ጉባኤው ባከናወናቸው መልካም ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ ጉባኤውን አመስግን። አድማጮች በነሐሴ ወር ያገኙት ጥሩ ተሞክሮ ካለ እንዲናገሩ ጋብዝ፤ አገልግሎቱን ለማስፋት ጥረት ላደረገ አንድ አስፋፊ ቃለ መጠይቅ አድርግ። በሚመጣው የአገልግሎት ዓመት ጉባኤው ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚችላቸውን አንድ ወይም ሁለት የአገልግሎት ዘርፎች በመጥቀስ እንዲሁም ማሻሻያ ለማድረግ የሚረዱ ተግባራዊ ሐሳቦችን በመናገር ክፍሉን ደምድም።
15 ደቂቃ፦ “ነቢያትን አርዓያ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው—ናሆም።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ።
መዝሙር 46 እና ጸሎት