የመስክ አገልግሎት ጎላ ያሉ ገጽታዎች
በታኅሣሥ 2014 በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከናወኑት አስደሳች ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዩ ጉባኤዎች የተውጣጡ 27 ወንድሞችና እህቶች የምልክት ቋንቋ ኮርስ ወስደው ታኅሣሥ ወር ላይ ተመርቀዋል። እነዚህ ተመራቂዎች በርካታ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት እንዲሰሙ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ እንተማመናለን።
በዚሁ ወር የጉባኤ ሽማግሌዎች ትምህርት ቤት ተካሂዶ ነበር። ከዚህ ቲኦክራሲያዊ ሥልጠና 104 የሚያህሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጥቅም እንዳገኙ መስማታችን አስደስቶናል። እነዚህ ሽማግሌዎች ያገኙት ሥልጠና በጉባኤያቸው ውስጥ ኃላፊነቶቻቸውን በሚወጡበት ጊዜ እንደሚረዳቸው እርግጠኞች ነን።