የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1
“ዛሬ ቤትዎ የመጣነው ሁላችንንም ስለሚያሳስበን አንድ ጉዳይ በአጭሩ ለመወያየት ነው። ከሚያጋጥሙን በጣም ከባድ ችግሮች መካከል አንዱ የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት ነው። እርስዎስ እንደዚህ ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን አንድ የሚያጽናና ተስፋ ላሳይዎት። [ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ በሞት ያጣናቸው የምንወዳቸው ሰዎች ከሞት የሚነሱበት ጊዜ እንደሚመጣ ይናገራል። ይህ መጽሔት፣ ይህ ተስፋ ፍጻሜውን የሚያገኘው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ነሐሴ
“በሴሎቻችን ውስጥ የተከማቸው መረጃ ምን ያህል ብዙ እንደሆነ በሚገልጽ አንድ ጽሑፍ ላይ ከጎረቤቶቻችን ጋር እየተወያየን ነበር። [የንቁ! መጽሔቱን የሽፋን ርዕስ አሳየው።] ብዙ ሰዎች ሕይወት የተገኘው በዝግመተ ለውጥ እንደሆነ ያምናሉ፤ ሌሎች ደግሞ በፍጥረት እንደሆነ ይናገራሉ። የእርስዎ አመለካከት ምንድን ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ መጽሔት አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ሕይወት ንድፍ አውጪ አለው? ብለው እንዲጠይቁ ያደረጉና ሴሎች ምን ያህል ውስብስብ እንደሆኑ የሚገልጹ ሐሳቦችን ይዟል።”