የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ፍላጎት እንዲኖራቸው እያበረታታን ነው። ብዙዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከዘመናዊው ሳይንስ አንጻር ሲታይ ትክክለኛ እንዳልሆነ ያምናሉ። እርስዎስ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይሰማዎታል? ትክክለኛ መረጃ የያዘ መጽሐፍ እንደሆነ ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ አንጻር ሲታይ ትክክለኛ እንደሆነ የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ልጥቀስልዎት። [ኢዮብ 26:7ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ሳይንስና መጽሐፍ ቅዱስ የሚስማሙት እንዲሁም የሚደጋገፉት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”
ንቁ! ሰኔ
“ብዙ ሰዎች ከበሽታ ጋር እየታገሉ ለመኖር ተገድደዋል፤ ዛሬ የመጣነው እነዚህን ሰዎች የሚያበረታታ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ልናሳይዎት ነው። [ኢሳይያስ 33:24ሀን አንብብ።] ሕመም የሚባል ነገር ባይኖር ኖሮ ሕይወታችን ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት ይችላሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ትንቢት ፍጻሜውን የሚያገኝበት ጊዜ እስኪደርስ ግን ጤንነታችንን ለማሻሻል የሚረዱ አምስት መሠረታዊ ነገሮች አሉ። ይህ መጽሔት እነዚህን ነገሮች ያብራራል።”