መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1
“ፈጣሪ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ ማወቅ የሚቻል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ አስደሳች ሐሳብ ባካፍልዎት ደስ ይለኛል።” በገጽ 16 ላይ ከ2ኛው ጥያቄ በታች ያለውን ሐሳብና አንዱን ጥቅስ አንብበህ ተወያዩባቸው። ከዚያም መጽሔቶቹን አበርክትለትና በጥያቄ 3 ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።
ንቁ! የካቲት 2011
“አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረ መጽሐፍ በመሆኑ ከሳይንስ አንጻር ትክክል እንዳልሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ብዙ ሰዎች በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ሲያነቡ ይገረማሉ። [ኢሳይያስ 40:22ን አንብብ።] በዚህ መጽሔት ገጽ 22 ላይ የሚገኘው ርዕስ ‘ሳይንስና መጽሐፍ ቅዱስ ይስማማሉ?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”
መጠበቂያ ግንብ መጋቢት 1
“የይሖዋ ምሥክሮች በሚያከናውኑት የስብከት ሥራ ይታወቃሉ። ይህን ሥራ የምናከናውነው ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እዚህ ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ልብ ይበሉ። [ማቴዎስ 24:14ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ‘ምሥራቹ ምንድን ነው?’ ‘መንግሥቱ ምንድን ነው?’ እና ‘እንደሚመጣ የተነገረው መጨረሻ ምንድን ነው?’ ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”
ንቁ! መጋቢት 2011
“ብዙዎቻችን ከበሽታ ጋር እየታገልን የምንኖር እንደመሆናችን መጠን ይህ ጥቅስ የያዘው ሐሳብ ሁላችንንም ያጽናናናል። [ኢሳይያስ 33:24ን አንብብ።] ይህ ተስፋ ፍጻሜውን ሲያገኝ ሕይወት ምን ያህል የሚለወጥ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አምላክ ይህንን ለውጥ እስከሚያመጣ ድረስ ሁላችንም ጤንነታችንን ለማሻሻል ልንወስዳቸው የምንችላቸው አንዳንድ መሠረታዊ እርምጃዎች አሉ። ይህ መጽሔት እነዚህን እርምጃዎች ያብራራል።”