መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 1
“በየቀኑ ለማለት ይቻላል ከጤናችን፣ ከቤተሰባችንና ከሥራችን ጋር የተያያዙ የተለያዩ ጥያቄዎች ያጋጥሙናል። ለእነዚህ ጥያቄዎች አስተማማኝና ተግባራዊ መልሶችን ማግኘት የምንችለው ከየት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ በ2 ጢሞቴዎስ 3:16 ላይ ምን እንደሚል ይመልከቱ። [ጥቅሱን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች እንዴት ሊረዳን እንደሚችል ያብራራል።”
ንቁ! ሚያዝያ 2007
“ብዙ ሰዎች ክርስቲያን እንደሆኑ ይናገራሉ። ክርስቲያን መሆን ሲባል ምን ማለት ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ኢየሱስ እዚህ ጥቅስ ላይ ምን እንዳለ ልብ ይበሉ። [ዮሐንስ 15:14ን አንብብ።] ይህ ርዕስ አንድ ሰው ክርስቲያን ነኝ ብሎ ከመናገር የበለጠ ነገር እንደሚያስፈልገው ይናገራል።” በገጽ 26 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
መጠበቂያ ግንብ ሚያዝያ 15
“በዛሬው ጊዜ የጭካኔ ድርጊቶችን መፈጸም እየተለመደ የመጣ ይመስላል። [በአካባቢው የተፈጸመን ወይም በመጽሔቱ ላይ የተጠቀሰን አንድ የጭካኔ ድርጊት እንደ ምሳሌ ጥቀስ።] ሰዎች እንዲህ ጨካኝ የሆኑት ለምን እንደሆነ ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ የጭካኔ ድርጊቶች እየተባባሱ እንደሚሄዱ የሚገልጽ ትንቢት ይዟል። [2 ጢሞቴዎስ 3:1-5ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ‘የጭካኔ ድርጊት የማይኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።”
ንቁ! ግንቦት 2007
“ጥቂት ሰዎች በብልጽግና ሲኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ በድህነት ይማቅቃሉ። በኑሮ ደረጃ መድልዎ የማይደረግበት ዓለም የምናይበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] አምላክ ለድሆች ምን አመለካከት እንዳለው ልብ ይበሉ። [መዝሙር 22:24ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ለድሆች የሚሰጠውን ተስፋ ያብራራል።”