መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
ማቴዎስ 24:3ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ በል፦ “አንዳንድ ሰዎች በዚህ ጥቅስ ላይ የቀረበው ጥያቄ የምድርን መጨረሻ አስመልክቶ የተጠየቀ ጥያቄ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምድር ትጠፋለች ብለው ያስባሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ኢየሱስ የሰጠው መልስ ወደፊት ይፈጸማል ብለን የምንጠብቀው የምድርን ሳይሆን የሌላ ነገር መጨረሻን እንደሆነ ይጠቁመናል። በገጽ 16 ላይ የሚጀምረው ርዕስ የሚጠፋው ምን እንደሆነ ማብራሪያ ይሰጣል።”
ንቁ! ግንቦት 2009
“አንዳንድ የሃይማኖት አስተማሪዎች አምላክን ደስ ካሰኘነው በቁሳዊ እንደሚያበለጽገን ሲሰብኩ ይሰማል። ይሁንና እርስዎ ድሃ የሆኑ ጥሩ ሰዎችን ያውቁ ይሆናል። አምላክ ሀብታም እንድንሆን የሚፈልግ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም ዕብራውያን 13:5ን አንብብ።] ይህ ርዕሰ ጉዳይ አምላክ እኛን የሚባርከው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።” በገጽ 12 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“ብዙ ሰዎች ስለ ልጅ አስተዳደግም ሆነ የተሳካ ቤተሰብ ስለ መመሥረት ምክር ቢያገኙ ደስ ይላቸዋል። እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ግሩም ምክር ከየት ማግኘት የምንችል ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] አብዛኞቹ ሰዎች ለአስተማማኝ ምክር ምንጭ ለሆነው ለሚከተለው ነገር እምብዛም ትኩረት አይሰጡም። [2 ጢሞቴዎስ 3:16ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በመጽሐፍ ቅዱስ መተማመን የምንችለው ለምን እንደሆነ ያብራራል፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክር እንደያዘ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ይዟል።”
ንቁ! ሰኔ 2009
“‘ፅንስ ማስወረድ ትክክል ነው ወይስ አይደለም?’ የሚለው ሐሳብ ከፍተኛ ክርክር የሚያስነሳ ጉዳይ እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው እንዲህ ያለ ምርጫ ቢደቀንበት ውሳኔ ለማድረግ እንደሚረዳው ይሰማዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። ከዚያም 2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17ን አንብብ።] ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ምን ሐሳብ እንደሚሰጥ ይናገራል።”