መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“ብዙ ሰዎች፣ የሚያምኑት የሚያዩትን ነገር ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ። እርስዎስ በእነዚህ ሰዎች አመለካከት ይስማማሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ሮሜ 1:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት በፍጥረት ላይ በግልጽ የምንመለከታቸውን ሦስት የአምላክ ባሕርያት ጎላ አድርጎ ይገልጻል። እንዲሁም ስለ እነዚህ ባሕርያት ማወቃችን በእኛ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል።”
ንቁ! ግንቦት 2008
“በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሰዎች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ማሰብ ያስፈራቸዋል። ሁኔታዎች እየተሻሻሉ የሚሄዱ ይመስልዎታል ወይስ እየተባባሱ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ራእይ 21:3, 4ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ የሰው ዘር ሊፈታቸው ያልቻላቸውን ከባድ ችግሮች አምላክ በቅርቡ እንደሚያስወግድ እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምን እንደሆነ ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“በጊዜያችን እየተከሰቱ ያሉት የተፈጥሮ አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መሄዳቸው፣ አንዳንድ ሰዎች ‘አምላክ እየቀጣን ይሆናል’ የሚል ስሜት እንዲያድርባቸው አድርጓል። እርስዎስ ምን ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም 1 ዮሐንስ 4:8ን አንብብ።] ይህ ርዕስ፣ የተፈጥሮ አደጋዎች ለሚያደርሱት ጉዳት አምላክ ተጠያቂ የማይሆነው ለምን እንደሆነ ያብራራል።” በገጽ 30 ላይ ያለውን ርዕስ አስተዋውቀው።
ንቁ! ግንቦት 2008
“ብዙዎች ስለሚያውቁት ስለዚህ ጥቅስ ያለዎትን አመለካከት ባውቅ ደስ ይለኛል። [ማቴዎስ 6:10ን አንብብ።] ‘አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?’ ብለው ጠይቀው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ከመጀመሪያው አንስቶ ለምድር ዓላማ እንደነበረውና ይህም ዓላማው እስካሁን ድረስ እንዳልተለወጠ ይገልጻል። ይህ ርዕስ ስለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ይዟል።” ገጽ 10 ላይ የሚጀምረውን ርዕስ አስተዋውቀው።