የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/13 ገጽ 4
  • የአቀራረብ ናሙናዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቀራረብ ናሙናዎች
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • የአቀራረብ ናሙና
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
km 1/13 ገጽ 4

የአቀራረብ ናሙናዎች

በወሩ የመጀመሪያ ቅዳሜ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አቀራረብ

“ብዙ ሰዎች ዲያብሎስ በዓለም ላይ ለሚደርሰው ክፋት ተጠያቂ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ያም ቢሆን ‘ዲያብሎስ የመጣው ከየት ነው? የፈጠረው አምላክ ነው?’ እያሉ ያስባሉ፤ እርስዎ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ይህን ርዕስ ይመልከቱ።” የየካቲት 1⁠ን መጠበቂያ ግንብ ስጠውና በመጨረሻ ገጽ ላይ ያለውን ዓምድ አሳየው። ከዚያም በመጀመሪያው ንዑስ ርዕስ ሥር ባለው ሐሳብ እና በዚያ ውስጥ በተጠቀሰው ጥቅስ ላይ ተወያዩ። መጽሔቶቹን ካበረከትክለት በኋላ በሚቀጥለው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ያዝ።

መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1

“ክርስቲያኖች፣ አይሁዳውያን እንዲሁም ሙስሊሞች ትልቅ ቦታ ስለሚሰጡት አንድ ሰው ብጠይቅዎት ደስ ይለኛል። ግለሰቡ ሙሴ ነው። ሙሴ የሚለውን ስም ሲሰሙ መጀመሪያ ወደ አእምሮዎ የሚመጣው ነገር ምንድን ነው? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ሙሴ ስህተት ሠርቶ የሚያውቅ ሰው ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ እሱን የሚገልጽበት መንገድ ትኩረት የሚስብ ነው። [ዘዳግም 34:10-12⁠ን አንብብ።] ይህ መጽሔት የሙሴን ሦስት ግሩም ባሕርያት የሚያጎላ ሲሆን እኛም ምሳሌውን መከተል የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።”

ንቁ! የካቲት

“በዛሬው ጊዜ ሰዎች የተሻለ ሕይወት ለመምራት በማሰብ ወደ ሌላ አገር መሰደዳቸው የተለመደ ነው። እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ ያሰቡትን ነገር የሚያገኙ ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እርግጥ ነው፣ ስደት በዚህ ዘመን ብቻ የተከሰተ ነገር አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ መጽሐፍ ላይ የሚገኝ አንድ ዘገባ ላሳይዎት። [ዘፍጥረት 46:5, 6⁠ን አንብብ። እንዲሁም በመጀመሪያው ርዕስ መጨረሻ ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎች አሳየው።] ይህ መጽሔት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ