ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | አስቴር 6-10
አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ በመቆርቆር እርምጃ ወስዳለች
በወረቀት የሚታተመው
አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ ጥብቅና ስትቆም ደፋርና የራሷን ጥቅም መሥዋዕት የምታደርግ መሆኗን አሳይታለች
አስቴርና መርዶክዮስ ከሞት ተርፈዋል። ይሁን እንጂ ሃማ አይሁዳውያንን በሙሉ ለመፍጀት ያወጣው አዋጅ በፋርስ ግዛት ውስጥ ከዳር እስከ ዳር እየተዳረሰ ነበር
አስቴር ለሁለተኛ ጊዜ ሕይወቷን አደጋ ላይ በመጣል ሳትጠራ ንጉሡ ፊት ቀረበች። ንጉሡ እግር ላይ ወድቃ ስለ ሕዝቧ በማልቀስ የወጣውን አሰቃቂ አዋጅ እንዲሽር ለመነች
በንጉሡ ስም የተላለፈ ሕግ ሊሻር አይችልም። ስለዚህ ንጉሡ አዲስ ሕግ እንዲያጸድቁ ለአስቴርና ለመርዶክዮስ ሥልጣን ሰጣቸው
ይሖዋ ለሕዝቡ ታላቅ ድል ሰጣቸው
አይሁዳውያን ራሳቸውን የመከላከል መብት እንዳላቸው የሚገልጽ ሁለተኛ አዋጅ ወጣ
ፈረሰኞች በግዛቱ ውስጥ ወዳሉት ስፍራዎች ሁሉ በፍጥነት ሄዱ፤ አይሁዳውያንም ለጦርነት ተዘጋጁ
ብዙ ሰዎች አምላክ አይሁዳውያንን እንደረዳቸው በመገንዘብ የአይሁድ እምነትን ተቀበሉ