የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb16 መስከረም ገጽ 3
  • ‘በይሖዋ ሕግ ተመላለሱ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘በይሖዋ ሕግ ተመላለሱ’
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በይሖዋ ቃል ታመኑ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • የአምላክ ቃል መንገዳችሁን እንዲያበራላችሁ ፍቀዱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ለአምላክ ቃል ያላችሁ ፍቅር ምን ያህል ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • “ሕግህን ምንኛ ወደድሁ!”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
mwb16 መስከረም ገጽ 3

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መዝሙር 119

‘በይሖዋ ሕግ ተመላለሱ’

በይሖዋ ሕግ መመላለስ ሲባል ለመለኮታዊ አመራር ራሳችንን በፈቃደኝነት ማስገዛት ማለት ነው። እንደ መዝሙራዊው ሁሉ የይሖዋን ሕግ በመከተልና በእሱ በመታመን ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን።

መዝሙራዊው ምርኩዝ ይዞ ሲሄድ

እውነተኛ ደስታ ማግኘታችን የተመካው በአምላክ ሕግ በመመራታችን ላይ ነው

119: 1-8

ኢያሱ አንድ ጥቅልል እያነበበ

ኢያሱ ይሖዋ በሚሰጣቸው መመሪያዎች ላይ ሙሉ እምነት እንዳለው አሳይቷል። ደስተኛና ስኬታማ መሆን የሚችለው በሙሉ ልቡ በይሖዋ ከታመነ ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር

የአምላክ ቃል በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን መከራዎች የምንቋቋምበት ድፍረት ይሰጠናል

119:33-40

ኤርምያስ ሲጸልይ

ኤርምያስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙትም ድፍረት እንዳለውና በይሖዋ እንደሚታመን አሳይቷል። ቀላል ሕይወት ይመራ የነበረ ከመሆኑም ሌላ የተሰጠውን ኃላፊነት በጽናት ተወጥቷል

ስለ አምላክ ቃል ትክክለኛ እውቀት ማግኘታችን በልበ ሙሉነት እንድንመሠክር ያደርገናል

119:41-48

ጳውሎስ ለአገረ ገዢው ለፊሊክስ ሲሰብክ

ጳውሎስ የአምላክን መልእክት ያለምንም ፍርሃት ለሁሉም ሰው ይሰብክ ነበር። ለአገረ ገዢው ለፊሊክስ በሰበከበት ወቅት ይሖዋ እንደሚረዳው ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነበር

መዝሙራዊው ምርኩዝ ይዞ ሲሄድ

ይበልጥ ድፍረት ማዳበር የሚያስፈልገኝ በየትኞቹ ሁኔታዎች ውስጥ ስመሠክር ነው?

  • በትምህርት ቤት

  • በሥራ ቦታ

  • ለቤተሰብ አባላት

  • በሌሎች ቦታዎች

መዝሙር 119 የተጻፈው በፊደል ቅደም ተከተል ነው። በዚህ መልኩ የተቀናበረው በቀላሉ ለማስታወስ እንዲረዳ ታስቦ ሊሆን ይችላል። ይህ መዝሙር እያንዳንዳቸው 8 ቁጥሮች በያዙ 22 ክፍሎች ተከፋፍሏል። በአንድ ክፍል ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ቁጥር የሚጀምረው በተመሳሳይ የዕብራይስጥ ፊደል ነው። የዕብራይስጥ ቋንቋ 22 ፊደላት ስላሉት ይህ መዝሙር በአጠቃላይ 176 ቁጥሮች አሉት፤ በመሆኑም ይህ መዝሙር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ሁሉ ረጅሙ መዝሙር ሊሆን ችሏል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ