የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—የካቲት 2017
ከየካቲት 6-12
it-1 643 አን. 4-5
ፍቺ
ምሳሌያዊ ፍቺ። ጋብቻ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ ተሠርቶበታል። (ኢሳ 54:1, 5, 6፤ 62:1-6) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምሳሌያዊ ፍቺ ወይም ሚስትን ስለ ማሰናበት ይናገራል።—ኤር 3:8
በ607 ዓ.ዓ. የይሁዳ መንግሥት የተገለበጠ ሲሆን ኢየሩሳሌምም ወደመች፤ በዚያ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች ወደ ባቢሎን በግዞት ተወሰዱ። ይሖዋ ወደፊት በግዞት ለሚወሰዱት አይሁዳውያን አስቀድሞ ትንቢት ተናግሮ ነበር፤ እንዲህ ብሏቸዋል፦ “እናታችሁን በሰደድኳት ጊዜ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ሰጥቻታለሁ?” (ኢሳ 50:1) ይሖዋ ‘እናታቸውን’ ማለትም ብሔሩን ያስወገደበት በቂ ምክንያት ነበረው፤ ይሖዋ ቃል ኪዳኑን በማጠፍ ፍቺ አልፈጸመም፤ እናታቸውን ያሰናበታት የሕጉን ቃል ኪዳን ባለማክበር ስህተት ስለፈጸመች ነው። ሆኖም ጥቂት እስራኤላውያን ንስሐ የገቡ ከመሆኑም ሌላ ይሖዋ ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመልሳቸውና ከእነሱ ጋር የነበረውን እንደ ባል ያለ ዝምድና እንዲያድስ ጸሎት አቅርበዋል። ይሖዋ ለስሙ ሲል፣ ቃል በገባው መሠረት ሕዝቡ ወደ ትውልድ አገሩ እንዲመለስ አድርጓል፤ ይህ የሆነው ኢየሩሳሌም ባድማ ሆና የምትቆይበት ሰባ ዓመት እንዳበቃ ማለትም በ537 ዓ.ዓ ነው።—መዝ 137:1-9፤ ጋብቻ የሚለውን ተመልከት።