የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 3 ገጽ 4-5
  • የሚወደን ፈጣሪያችን ያስብልናል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሚወደን ፈጣሪያችን ያስብልናል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1. ፈጣሪያችን ፀሐይን ያወጣል
  • 2. ፈጣሪያችን ዝናብ ያዘንባል
  • 3. ፈጣሪያችን ምግብና ልብስ ይሰጠናል
  • ዝናብ በመኖሩ አመስጋኝ ሁን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ቁሳዊ ነገሮችን ሳይሆን የአምላክን መንግሥት ፈልጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • ፈጣሪህ ምን ዓይነት አምላክ እንደሆነ ተማር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ሁሉንም ነገሮች የሠራው ፈጣሪ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 3 ገጽ 4-5
ፀሐይ ከተራሮቹ በላይ ከፍ ብላ እየወጣች።

የሚወደን ፈጣሪያችን ያስብልናል

1. ፈጣሪያችን ፀሐይን ያወጣል

የፀሐይ ብርሃን ባይኖር ኖሮ ሕይወት ምን እንደሚመስል መገመት ትችላለህ? ዛፎች ቅጠልና አበባ ለማውጣት እንዲሁም ፍሬ ለማፍራትና ዘር ለማስገኘት የሚያስችላቸውን ኃይል የሚያገኙት ከፀሐይ ነው። በተጨማሪም ከፀሐይ የሚገኘው ኃይል፣ ዛፎች በሥሮቻቸው አማካኝነት ከአፈር ውስጥ ውኃ መሳብና ወደ ቅጠሎቻቸው ማድረስ እንዲችሉ ያደርጋል፤ በዛፎቹ ቅጠሎች ላይ ያለው ውኃ እንዲተን የሚያደርገውም የፀሐይ ኃይል ነው።

በተራራ ላይ ያለ ለምለም የሻይ ቅጠል ተክል ከላይ ሲታይ።

2. ፈጣሪያችን ዝናብ ያዘንባል

ዝናብ ከአምላክ ያገኘነው ውድ ስጦታ ነው፤ ምድራችን የምንመገበውን ምግብ ማብቀል የምትችለው በዝናብ ውኃ ነው። አምላክ ከሰማይ ዝናብ በማዝነብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት እንዲሁም የተትረፈረፈ ምግብ በማቅረብ ልባችንን በደስታ ይሞላዋል።

በአንድ ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ያረፈች ወፍ፤ አንድ ፍሬ ለመብላት አፏን ከፍታለች።

3. ፈጣሪያችን ምግብና ልብስ ይሰጠናል

ብዙ አባቶች ለቤተሰባቸው በቂ ምግብና ልብስ የማቅረብ ጉዳይ ያስጨንቃቸዋል። ቅዱሳን መጻሕፍት ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚሉ እንመልከት፦ “የሰማይ ወፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ እነሱ አይዘሩም፣ አያጭዱም ወይም በጎተራ አያከማቹም፤ ይሁንና በሰማይ ያለው አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከእነሱ አትበልጡም?”—ማቴዎስ 6:25, 26

“እስቲ የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤ . . . ያን ያህል ክብር የነበረው [ንጉሥ] ሰለሞን እንኳ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዷ አላጌጠም። አምላክ . . . የሜዳ [ተክልን] እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ . . . እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም?”—ማቴዎስ 6:28-30

አምላክ ምግብና ልብስ ሊሰጠን የሚችል ከሆነ ለሕይወት የሚያስፈልጉንን ሌሎች ነገሮችም ለማግኘት እንደሚረዳን ልንጠራጠር አይገባም። የእሱን ፈቃድ እስካደረግን ድረስ አምላክ፣ አርሰን ምግባችንን ለማምረት የምናደርገውን ጥረት ይባርክልናል፤ አሊያም የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለመግዛት የሚያስችለንን ሥራ እንድናገኝ ይረዳናል።—ማቴዎስ 6:32, 33

በእርግጥም ስለ ፀሐይ፣ ስለ ዝናብ፣ ስለ ወፎችና ስለ አበቦች ስናስብ አምላክን ለመውደድ እንነሳሳለን። በቀጣዩ ርዕስ ላይ ፈጣሪ ለሰው ልጆች መልእክት ያስተላለፈው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

ፈጣሪያችን “ፀሐዩን ያወጣል . . . ዝናብ ያዘንባል።”—ማቴዎስ 5:45

ፈጣሪያችን በጣም ይወደናል እንዲሁም ያስብልናል። ልጆቹን እንደሚወድ አንድ አባት ሁሉ ፈጣሪያችንም ቤተሰቡን ይንከባከባል። ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ፈጣሪ ሲናገሩ ‘ገና ሳንለምነው ምን እንደሚያስፈልገን የሚያውቅ’ ለጋስ አምላክ እንደሆነ ይገልጻሉ።—ማቴዎስ 6:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ