የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 3 ገጽ 14-15
  • ፈጣሪያችን ያዘጋጃቸውን ዘላለማዊ በረከቶች ማግኘት ትችላለህ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፈጣሪያችን ያዘጋጃቸውን ዘላለማዊ በረከቶች ማግኘት ትችላለህ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከኢየሱስ ተአምራት ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ከኢየሱስ ተአምራት ምን እንማራለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • የሰው ልጆችን ይወዳል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተአምራት እውነተኛ ታሪክ ናቸው ወይስ ምናባዊ ፈጠራ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 3 ገጽ 14-15
የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች ገነት በሆነችው ምድር ላይ በደስታ አብረው ጊዜ ሲያሳልፉ።

“ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤ አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።”—መዝሙር 67:6

ፈጣሪያችን ያዘጋጃቸውን ዘላለማዊ በረከቶች ማግኘት ትችላለህ

አምላክ ለነቢዩ አብርሃም ከዘሮቹ መካከል አንዱ ‘ለምድር ብሔራት ሁሉ’ በረከት እንደሚያመጣ ቃል ገብቶለት ነበር። (ዘፍጥረት 22:18) ታዲያ ይህ የአብርሃም ዘር ማን ነው?

ወደ 2,000 ከሚጠጉ ዓመታት በፊት፣ አምላክ የአብርሃም ዘር ለሆነው ለኢየሱስ ታላላቅ ተአምራትን የመፈጸም ኃይል ሰጥቶት ነበር። እነዚህ ተአምራት፣ አምላክ ለአብርሃም ቃል በገባው መሠረት ብሔራት የሚባረኩት በኢየሱስ በኩል እንደሆነ ይጠቁማሉ።—ገላትያ 3:14

ኢየሱስ የፈጸማቸው ተአምራት፣ ለሰው ልጆች በረከት ለማምጣት በአምላክ የተመረጠው እሱ መሆኑን አረጋግጠዋል፤ በተጨማሪም አምላክ በኢየሱስ ተጠቅሞ የሰው ልጆችን ለዘላለም የሚባርከው በምን መንገድ እንደሆነ አሳይተዋል። ኢየሱስ ያከናወናቸው ተአምራት የእሱን ግሩም ባሕርያት የሚያሳዩት እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

አዛኝ—ኢየሱስ የታመሙትን ፈውሷል።

በሥጋ ደዌ የተያዘ አንድ ሰው “ብትፈልግ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ኢየሱስን ለምኖት ነበር። ኢየሱስም ሰውየውን ዳሰሰውና “እፈልጋለሁ! ንጻ” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ የሥጋ ደዌው ለቀቀው።—ማርቆስ 1:40-42

ለጋስ—ኢየሱስ የተራቡትን መግቧል።

ኢየሱስ ሰዎች እንዲራቡ አይፈልግም ነበር። ጥቂት ዳቦና ዓሣ ተጠቅሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በተአምር የመገበባቸው ወቅቶች ነበሩ። (ማቴዎስ 14:17-21፤ 15:32-38) ሁሉም በልተው ጠግበዋል፤ እንዲያውም ብዙ ምግብ ተርፎ ነበር።

ሩኅሩኅ—ኢየሱስ የሞቱትን አስነስቷል።

ጧሪ ቀባሪ የሚሆናትን አንድ ልጇን በሞት ላጣችው መበለት ‘በጣም ስላዘነላት’ ልጇን ከሞት አስነስቶላታል።—ሉቃስ 7:12-15

ወደፊት በምድር ላይ የምናገኛቸው ዘላለማዊ በረከቶች

ኢየሱስ ያከናወናቸው ነገሮች፣ አምላክ ለሰው ልጆች በረከት ለማምጣት የሚያስችል ኃይል እንዳለው አሳይተዋል። ኢየሱስ፣ ቃል በገባው መሠረት በቅርቡ ተመልሶ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በኢየሱስ ተጠቅሞ በመላው ምድር ላይ እጅግ የላቁ ተአምራትን ያከናውናል።

አምላክ ለአብርሃም የገባውን ቃል ሲፈጽም በምድር ላይ ሕይወት ምን ይመስላል? አምላክን የሚወዱና የሚያከብሩ ሰዎች “ምድርን ይወርሳሉ፤ በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።” (መዝሙር 37:11) በዚያን ጊዜ “ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ . . . አይኖርም።”—ራእይ 21:4

ሰላም በሰፈነበት ምድር ላይ ለዘላለም መኖር እንዴት አስደሳች ይሆናል! በቅርቡ አምላክ ምድርን በሚገዛበት ወቅት ስለሚኖሩት በረከቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት www.jw.org/am​ን እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ