የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp20 ቁጥር 3 ገጽ 13
  • የተቸገሩትን የሚረዱ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተቸገሩትን የሚረዱ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ?
  • የተቸገሩትን መርዳት ሲባል ምን ማለት ነው?
  • “ደጉ ሳምራዊ” የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ይሖዋ የሚሰጥህን እርዳታ ትቀበላለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ዘረኝነት—መፍትሔው ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ‘በአምላክ ዘንድ ሀብታም’ ነህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
wp20 ቁጥር 3 ገጽ 13
አንድ ሰው ካርታ ተጠቅሞ ለሌላ ሰው አቅጣጫ ሲጠቁም።

ዕድሜ፣ ብሔር ወይም ሃይማኖት ሳትለይ ሁሉንም ሰዎች ትረዳለህ?

የተቸገሩትን የሚረዱ ሰዎች የሚያገኟቸው በረከቶች

በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ ሰዎች ምግብና መጠለያ አጥተው ይቸገራሉ። አንዳንዶች ደግሞ የወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ሆኖ አይታያቸውም። ታዲያ እንዲህ ያሉ ሰዎችን መርዳታችን የአምላክን ሞገስና በረከት የሚያስገኝልን እንዴት ነው?

ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ?

“ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤ ላደረገውም ነገር ብድራት ይከፍለዋል።”—ምሳሌ 19:17

የተቸገሩትን መርዳት ሲባል ምን ማለት ነው?

ኢየሱስ የተናገረውን አንድ ምሳሌ እስቲ እንመልከት፤ ዘራፊዎች አንድን ሰው ደብድበው በሕይወትና በሞት መካከል ትተውት ሄዱ። (ሉቃስ 10:29-37) አንድ መንገደኛ በዚያ በኩል ሲያልፍ፣ ጉዳት የደረሰበትን ይህን ሰው አየውና ወስዶ ተንከባከበው። ሰውየው ሌላ ዘር ያለው መሆኑ ደግነት ከማሳየት ወደኋላ እንዲል አላደረገውም።

ይህ ደግ ሰው፣ ጉዳት የደረሰበትን ሰው ቁስል በማከምና የሚያስፈልገውን ነገር በመስጠት ሥቃዩ እንዲቀልለት አድርጓል።

ከዚህ ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን? ኢየሱስ ይህን ምሳሌ የተናገረው፣ የተቸገሩ ሰዎችን በምንችለው መንገድ ሁሉ መርዳት እንዳለብን ለማስተማር ነው። (ምሳሌ 14:31) ቅዱሳን መጻሕፍት፣ አምላክ በቅርቡ ድህነትንና ሥቃይን እንደሚያስወግድ ያስተምራሉ። ሆኖም አምላክ ይህን የሚያደርገው እንዴትና መቼ እንደሆነ ጥያቄ ይፈጠርብን ይሆናል። የሚወድህ ፈጣሪ ስላዘጋጀልህ በረከቶች በቀጣዩ ርዕስ ላይ እንመለከታለን።

“አምላክ መቼም ቢሆን ትቶኝ አያውቅም”!

ከጋምቢያ የመጣ ስደተኛ የተናገረው

“ወደ አውሮፓ በመጣሁበት ወቅት ሥራ፣ ገንዘብም ሆነ ቤት በአጠቃላይ ምንም ነገር አልነበረኝም። በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ያሉት ሐሳቦች ብልህ እንድሆን፣ ጠንክሬ እንድሠራ እንዲሁም የሌሎችን እርዳታ ከመጠየቅ ይልቅ እኔ ራሴ ሌሎችን እንድረዳ አስተምረውኛል። አምላክ መቼም ቢሆን ትቶኝ አያውቅም፤ የእሱን በረከት በሕይወቴ አይቻለሁ!”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ