ከኅዳር 26–ታኅሣሥ 2
የሐዋርያት ሥራ 6-8
መዝሙር 124 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“አዲስ የተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ ተፈተነ”፦ (10 ደቂቃ)
ሥራ 6:1—ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ መበለቶች በጉባኤው ውስጥ ችላ ተብለው ነበር (bt 41 አን. 17)
ሥራ 6:2-7—ሐዋርያት ችግሩን ለመፍታት እርምጃ ወሰዱ (bt 42 አን. 18)
ሥራ 7:58–8:1—በጉባኤው ላይ ከባድ ስደት ተነሳ
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሥራ 6:15—የእስጢፋኖስ ፊት “እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ታያቸው” ሲባል ምን ማለት ነው? (bt 45 አን. 2)
ሥራ 8:26-30—በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች ፊልጶስ ባከናወነው ዓይነት ሥራ የመካፈል መብት ያገኙት እንዴት ነው? (bt 58 አን. 16)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሥራ 6:1-15
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም ግለሰቡ በስብሰባ ላይ እንዲገኝ ጋብዝ።
ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ ላይ ላነሳኸው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ጥቅስ መርጠህ ተጠቀም፤ ከዚያም አንድ የማስጠኛ ጽሑፍ አበርክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) lv 33 አን. 16-17
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ”፦ (15 ደቂቃ) አንድ ሽማግሌ በውይይት የሚያቀርበው። “ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ” የሚለውን ቪዲዮ በማጫወት ጀምር። ቅርንጫፍ ቢሮው ባለፈው የአገልግሎት ዓመት ከጉባኤው ለተላከለት መዋጮ የላከውን የምስጋና ደብዳቤ አንብብ። ከምናደርገው መዋጮ ምን ጥቅሞች እንደምናገኝ ጥቀስ። የጉባኤያችሁን ወርኃዊ ወጪዎች ተናገር። መዋጮ ማድረግ የምንችልባቸውን መንገዶች እንዲሁም መዋጮው እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ተወያዩበት። የጉባኤውን አባላት በልግስና ለሚያደርጉት መዋጮ አመስግናቸው።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 36
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 119 እና ጸሎት