ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ልጆቻችንን እንዴት እንደምናሳድግ አስተምሮናል
ወላጆች ከሰማያዊው አባታቸው ከይሖዋ የሚያገኙት ትምህርት ልጆቻቸውን ጥሩ አድርገው ለማሳደግ የሚረዳቸው እንዴት ነው? ይሖዋ ልጆቻችንን እንዴት እንደምናሳድግ አስተምሮናል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም ከአቢሊዮ እና ኡላ አሞሪም ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የአቢሊዮና የኡላ የልጅነት ሕይወት ምን ይመስል ነበር? ይህስ እነሱ ጥሩ ወላጆች እንዲሆኑ የረዳቸው እንዴት ነው?
ልጆቻቸው ስለ ልጅነት ሕይወታቸው ምን ዓይነት አስደሳች ትዝታ አላቸው?
አቢሊዮና ኡላ በዘዳግም 6:6, 7 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በተግባር ለማዋል ምን ዓይነት ጥረት አድርገዋል?
ለልጆቻቸው እንዲሁ ሕጎችን ከማውጣት ባለፈ ምን አድርገዋል?
እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን በሕይወታቸው ውስጥ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርጉ የረዷቸው እንዴት ነው?
አቢሊዮና ኡላ ልጆቻቸውን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንዲካፈሉ ምንጊዜም ያበረታቷቸው ነበር፤ እነዚህ ወላጆች ምን ዓይነት መሥዋዕት ከፍለዋል? (bt 178 አን. 19)