ክርስቲያናዊ ሕይወት
በኩዊቤክ ለሥራው ሕጋዊ መሠረት መጣል
ጳውሎስ ለፍርድ በቀረበበት ወቅት ወደ ቄሳር ይግባኝ ብሏል። የሮም ዜግነት ያለው መሆኑ ያስገኘለትን መብት በዚህ መንገድ መጠቀሙ ለእኛም ምሳሌ የሚሆን ነው። በኩዊቤክ ለሥራው ሕጋዊ መሠረት መጣል የሚለውን ቪዲዮ መመልከትህ፣ ወንድሞች በኩዊቤክ ለምሥራቹ ለመሟገት ሕጋዊ መብታቸውን የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ይረዳሃል። ቪዲዮውን ካየህ በኋላ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ስጥ፦
በኩዊቤክ የሚኖሩ ወንድሞቻችን ምን ዓይነት ተፈታታኝ ሁኔታዎች አጋጥመዋቸው ነበር?
ወንድሞች የትኛውን ትራክት አሰራጩ? ውጤቱስ ምን ሆነ?
ወንድም ኤመ ቡሼ ምን አጋጠመው?
የካናዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወንድም ቡሼ ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ?
ወንድሞች ከወንድም ቡሼ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የትኛውን ዝግጅት ተጠቀሙ? ውጤቱስ ምን ሆነ?
በቀሳውስት አነሳሽነት ፖሊሶች አንድን ክርስቲያናዊ ስብሰባ ማስተጓጎላቸው ምን አስከተለ?