ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 25-26
ጳውሎስ ወደ ቄሳር ይግባኝ አለ፤ ከዚያም ለንጉሥ ሄሮድስ አግሪጳ መሠከረ
“በገዢዎችና በነገሥታት ፊት” ብንቀርብ ምን ብለን እንደምንናገር መጨነቅ ባይኖርብንም፣ ስለ ተስፋችን ምክንያት እንድናቀርብ ለሚጠይቀን ሰው ሁሉ “መልስ ለመስጠት ዘወትር ዝግጁ” መሆን ያስፈልገናል። (ማቴ 10:18-20፤ 1ጴጥ 3:15) ተቃዋሚዎች “በሕግ ስም ችግር ለመፍጠር” በሚያሴሩበት ጊዜ የጳውሎስን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?—መዝ 94:20
ሕጋዊ መብታችንን በመጠቀም ለምሥራቹ እንሟገታለን።—ሥራ 25:11
ባለሥልጣናትን በምናነጋግርበት ጊዜ አክብሮት እናሳያለን።—ሥራ 26:2, 3
ሁኔታው አመቺ ከሆነ ምሥራቹ እኛንም ሆነ ሌሎችን እንዴት እንደጠቀመ እንናገራለን።—ሥራ 26:11-20