ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 23-24
ዓመፅ አነሳሽና መቅሰፍት ተብሎ ተከሰሰ
በኢየሩሳሌም የነበሩት አይሁዳውያን ጳውሎስን “እስኪገድሉ ድረስ እህል ውኃ ላለመቅመስ ተማማሉ።” (ሥራ 23:12 ግርጌ) የይሖዋ ዓላማ ግን ጳውሎስ ወደ ሮም ሄዶ ምሥክርነት እንዲሰጥ ነበር። (ሥራ 23:11) የጳውሎስ እህት ልጅ ሴራቸውን ስለሰማ ጉዳዩን ለጳውሎስ ነገረው፤ በመሆኑም ጳውሎስ ከሞት ተረፈ። (ሥራ 23:16) ይህ ዘገባ ስለሚከተሉት ነገሮች ምን ያስተምርሃል?
የአምላክን ዓላማ ለማጨናገፍ ስለሚደረግ ሙከራ
አምላክ እኛን ለመርዳት ስለሚጠቀምበት መንገድ
ድፍረት ስለማሳየት