የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 መስከረም ገጽ 7
  • እነዚህን ነገሮች “ማሰባችሁን አታቋርጡ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እነዚህን ነገሮች “ማሰባችሁን አታቋርጡ”
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፊልጵስዩስ 4:8—“እውነት የሆነውን ነገር ሁሉ . . . ማሰባችሁን አታቋርጡ”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • በአስተሳሰብ ንጹሕ አቋምን መጠበቅ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • በልቤ የማሰላስለው ነገር
    ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’
  • በእምነታችን ላይ በጎነትን መጨመር የምንችለው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 መስከረም ገጽ 7
አንድ ወንድም ሌሊት ኮምፒውተር እየተጠቀመ፤ በአንበሳ የተመሰለው ሰይጣን አጠገቡ ቆሟል

ክርስቲያናዊ ሕይወት

እነዚህን ነገሮች “ማሰባችሁን አታቋርጡ”

የትኞቹን ነገሮች? ፊልጵስዩስ 4:8 እውነት የሆነውን፣ ቁም ነገር ያለበትን፣ ጽድቅ የሆነውን፣ ንጹሕ የሆነውን፣ ተወዳጅ የሆነውን፣ በመልካም የሚነሳውን፣ በጎ የሆነውንና ምስጋና የሚገባውን ነገር እንድናስብ ያበረታታናል። እርግጥ ነው፣ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ስለ መንፈሳዊ ነገሮች ብቻ እንዲያስቡ አይገደዱም። ያም ቢሆን በልባችን የምናሰላስለው ነገር ይሖዋን ሊያስደስተው ይገባል። አስተሳሰባችን ለአምላክ ታማኝ ለመሆን ያደረግነውን ቁርጥ ውሳኔ ሊያዳክምብን አይገባም።—መዝ 19:14

ከመጥፎ ሐሳቦች መራቅ ቀላል አይደለም። ምክንያቱም ፍጹም ካልሆነው ሥጋችን ጋር ብቻ ሳይሆን “የዚህ ሥርዓት አምላክ” ከሆነው ከሰይጣን ጋርም መታገል ይጠበቅብናል። (2ቆሮ 4:4) በዓለማችን ውስጥ ያለውን መገናኛ ብዙኃን የሚቆጣጠረው ሰይጣን ስለሆነ በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በኢንተርኔትና በጽሑፎች የሚገኘው አብዛኛው ነገር ወራዳ ነው። ወደ አእምሯችን በምናስገባቸው ነገሮች ረገድ ጠንቃቆች ካልሆንን አስተሳሰባችን ይበከላል፤ ውሎ አድሮ ደግሞ መጥፎ ድርጊት ልንፈጽም እንችላለን።—ያዕ 1:14, 15

ታማኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን አስወግዱ—ተገቢ ያልሆነ መዝናኛ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንድ ወንድም ሌሊት ላይ ተገቢ ያልሆነ ነገር በስልኩ ሲመለከት

    ወንድም በስልኩ ላይ የሚያየው ምን ነበር? ምን ተጽዕኖስ አሳድሮበታል?

  • አንድ ወንድም የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቱን ሲዘጋ

    በገላትያ 6:7, 8 እና በመዝሙር 119:37 ላይ ያለው ሐሳብ ወንድምን የረዳው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ