ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ያዕቆብ 1-2 ወደ ኃጢአትና ወደ ሞት የሚመራው መንገድ 1:14, 15 መጥፎ ሐሳቦች ወደ አእምሮህ ሲመጡ እንዲህ አድርግ፦ ስለ ሌላ ነገር ለማሰብ ጥረት አድርግ።—ፊልጵ 4:8 በፈተናው መሸነፍ የሚያስከትለውን መዘዝ አስብ።—ዘዳ 32:29 ጸልይ።—ማቴ 26:41 መጥፎ ሐሳቦችን ከአእምሮህ ለማስወጣት በየትኞቹ የሚያንጹ ነገሮች ላይ ማተኮር ትችላለህ?