ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 6-8
“ልክ እንደዚሁ አደረገ”
ምንም ዓይነት ዘመናዊ የግንባታ መሣሪያም ሆነ ዘመናዊ የግንባታ ዘዴ ባልነበረበት በዚያ ወቅት መርከብ መገንባት ለኖኅና ለቤተሰቡ ምን ያህል ከባድ ሊሆንባቸው እንደሚችል ለማሰብ ሞክር።
መርከቡ በጣም ትልቅ ነበር—ርዝመቱ 133 ሜትር፣ ወርዱ 22 ሜትር፣ ከፍታው ደግሞ 13 ሜትር ገደማ ይሆናል
ዛፎችን መቁረጥ፣ በተፈለገው ልክ ማስተካከልና አንስቶ ወደ ግንባታ ቦታው መውሰድ ያስፈልግ ነበር
ይህ ግዙፍ መርከብ ውስጡም ሆነ ውጭው በቅጥራን መለቅለቅ ነበረበት
ለኖኅ ቤተሰብም ሆነ ለእንስሳቱ ለአንድ ዓመት ያህል የሚበቃ ምግብ መጠራቀም ነበረበት
ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ ከ40 እስከ 50 ዓመት ሳይፈጅ አይቀርም
ይሖዋ ያዘዘንን ነገር ማድረግ ተፈታታኝ ሲሆንብን ይህን ዘገባ ማስታወሳችን የሚረዳን እንዴት ነው?