ከጥር 20-26
ዘፍጥረት 6-8
መዝሙር 89 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
• ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ልክ እንደዚሁ አደረገ”፦ (10 ደቂቃ)
ዘፍ 6:9, 13—ጻድቅ የሆነው ኖኅ የሚኖረው በክፉዎች መካከል ነበር (w18.02 4 አን. 4)
ዘፍ 6:14-16—ኖኅ ተፈታታኝ ሥራ ተሰጥቶት ነበር (w13 4/1 14 አን. 1)
ዘፍ 6:22—ኖኅ በይሖዋ እንደሚታመን አሳይቷል (w11 9/15 18 አን. 13)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (10 ደቂቃ)
ዘፍ 7:2—ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው፣ ንጹሕ የሆኑና ያልሆኑ እንስሳትን ለመለየት የተሠራበት መሥፈርት ምንድን ነው? (w04 1/1 29 አን. 7)
ዘፍ 7:11—ዓለምን ያጥለቀለቀው ውኃ የመጣው ከየት ነው ብሎ መደምደሙ ምክንያታዊ ይሆናል? (w04 1/1 30 አን. 1)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋ አምላክን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
• በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ አስፋፊዋ ለቤቱ ባለቤት 1 ዮሐንስ 4:8ን ያብራራችላት እንዴት ነው? አስፋፊዎቹ ምሥክርነት ሲሰጡ ተባብረው የሠሩት እንዴት ነው?
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም። (th ጥናት 12)
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ከዚያም በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ከሚገኙት ጽሑፎች አንዱን አበርክት። (th ጥናት 7)
• ክርስቲያናዊ ሕይወት
የቤተሰብ አምልኮ፦ ኖኅ አካሄዱን ከአምላክ ጋር አድርጓል፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦ በዚህ ቪዲዮ ላይ ያየናቸው ወላጆች ስለ ኖኅ የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ልጆቻቸውን ለማስተማር የተጠቀሙበት እንዴት ነው? በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት ልትጠቀሙበት የምትችሉት ምን ጠቃሚ ሐሳብ አገኛችሁ?
ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ፦ (5 ደቂቃ)
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 91
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
መዝሙር 151 እና ጸሎት