ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 38–39
ይሖዋ ዮሴፍን ፈጽሞ አልተወውም
ዮሴፍ ባሳለፋቸው በመከራ የተሞሉ ጊዜያት ይሖዋ ‘የሚሠራውን ነገር ሁሉ ያሳካለት’ ከመሆኑም ሌላ ‘በእስር ቤቱ አለቃ ፊት ሞገስ ሰጥቶታል።’ (ዘፍ 39:2, 3, 21-23) ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?
መከራ የሚደርስብን የይሖዋን ሞገስ ስላጣን አይደለም።—መዝ 34:19
ይሖዋ እየባረከን ያለው እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ጥረት ማድረግና አመስጋኝ መሆን አለብን።—ፊልጵ 4:6, 7
ድጋፍ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ዞር ማለት ይኖርብናል።—መዝ 55:22