ክርስቲያናዊ ሕይወት
እንደ ዮሴፍ ከሥነ ምግባር ብልግና ሽሹ
የፆታ ብልግና እንድንፈጽም የሚገፋፋ ፈተና ሲያጋጥመን ዮሴፍ ጥሩ ምሳሌ ይሆነናል። የጌታው ሚስት በተደጋጋሚ ልታባብለው ብትሞክርም ግብዣዋን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም። (ዘፍ 39:7-10) ዮሴፍ “እንዲህ ያለውን እጅግ መጥፎ ድርጊት በመፈጸም በአምላክ ላይ እንዴት ኃጢአት እሠራለሁ?” በማለት የሰጠው ምላሽ ይሖዋ ለትዳር ጓደኛ ታማኝ ስለመሆን ያለውን አመለካከት አስቀድሞ እንዳሰበበት ይጠቁማል። ፈተናው አፍጥጦ በመጣበት ጊዜ ደግሞ እዚያው ቆይቶ አቋሙን እንዲያላላ የሚያደርግ ሁኔታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ከአካባቢው መሸሽ መርጧል።—ዘፍ 39:12፤ 1ቆሮ 6:18
ከሥነ ምግባር ብልግና ሽሹ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ጂን ምን ዓይነት ሁኔታ አጋጥሞታል?
ጂን፣ ሚክዮንግ የሒሳብ የቤት ሥራዋን በመሥራት እንዲያግዛት በጠየቀችው ጊዜ ምን ብሎ ማሰብ ጀመረ?
ሚክዮንግ ያቀረበችው ጥያቄ በጂን ላይ ምን ስሜት አሳድሮበታል?
ጂን እርዳታ ለማግኘት ምን እርምጃ ወስዷል?
ጂን ከሥነ ምግባር ብልግና ለመሸሽ ምን አድርጓል?
ከዚህ ቪዲዮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?