ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፍጥረት 40–41
ይሖዋ ዮሴፍን ታደገው
ይሖዋ ዮሴፍን የታደገው ዮሴፍ ለ13 ዓመት ገደማ በባርነትና በእስር ብዙ መከራ ካሳለፈ በኋላ ነው። ዮሴፍ ግን በምሬት ከመሞላት ይልቅ የደረሰበት መከራ የተሻለ ሰው እንዲያደርገው ፈቅዷል። (መዝ 105:17-19) ይሖዋ ፈጽሞ እንዳልተወው እርግጠኛ ነበር። ዮሴፍ ባለበት ሁኔታ ሥር አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ያደረገው እንዴት ነው?
ትጉና እምነት የሚጣልበት እንደሆነ አሳይቷል፤ ይህም ይሖዋ እሱን የሚባርክበት ነገር እንዲያገኝ አስችሏል።—ዘፍ 39:21, 22
በደል የፈጸሙበትን ሰዎች ለመበቀል ከማሴር ይልቅ ለሌሎች ደግነት አሳይቷል።—ዘፍ 40:5-7
የዮሴፍ ታሪክ በሕይወቴ ውስጥ የሚያጋጥሙኝን ችግሮች ለመቋቋም የሚረዳኝ እንዴት ነው?
ይሖዋ በአርማጌዶን እስኪታደገኝ ድረስ፣ ባለሁበት ሁኔታ ሥር አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?