የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp25 ቁጥር 1 ገጽ 9
  • ጦርነት እና ግጭት ሊቆም ያልቻለው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጦርነት እና ግጭት ሊቆም ያልቻለው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኃጢአት
  • የዓለም መንግሥታት
  • ሰይጣንና አጋንንቱ
  • ጦርነት እና ግጭት የሚቀረው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
  • አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • አዳምና ሔዋን የሠሩት ኃጢአት ምን ነበር?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ጦርነት እና ግጭት ሁላችንንም የሚነካን እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2025
wp25 ቁጥር 1 ገጽ 9

ጦርነት እና ግጭት ሊቆም ያልቻለው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የጦርነትና የግጭት ዋነኛ መንስኤዎች ምን እንደሆኑ እንዲሁም ጦርነት እስካሁን ሊቆም ያልቻለው ለምን እንደሆነ ይገልጽልናል።

ኃጢአት

አምላክ የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን አዳምንና ሔዋንን የፈጠራቸው በራሱ መልክ ነው። (ዘፍጥረት 1:27) በመሆኑም ሰላምንና ፍቅርን ጨምሮ የአምላክን ባሕርያት የማንጸባረቅ ተፈጥሯዊ ችሎታ ነበራቸው። (1 ቆሮንቶስ 14:33፤ 1 ዮሐንስ 4:8) ሆኖም አዳምና ሔዋን አምላክን ሳይታዘዙ ቀሩ፤ እንዲሁም ኃጢአት ሠሩ። በዚህም የተነሳ ሁላችንም ኃጢአትንና ሞትን ወርሰናል። (ሮም 5:12) በዘር የወረስነው ኃጢአት አስተሳሰባችንም ሆነ ድርጊታችን ወደ ዓመፅ ያዘነበለ እንዲሆን አድርጓል።—ዘፍጥረት 6:5፤ ማርቆስ 7:21, 22

የዓለም መንግሥታት

አምላክ ሲፈጥረን ራሳችንን በራሳችን የማስተዳደር ችሎታ አልሰጠንም። መጽሐፍ ቅዱስ “[ሰው] አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም” ይላል። (ኤርምያስ 10:23) በዚህም የተነሳ የዓለም መንግሥታት ጦርነትንና ዓመፅን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት አይችሉም።

ሰይጣንና አጋንንቱ

መጽሐፍ ቅዱስ ‘መላው ዓለም በክፉው ቁጥጥር ሥር እንደሆነ’ ይናገራል። (1 ዮሐንስ 5:19) “ክፉው” የተባለው ሰይጣን ዲያብሎስ ነው፤ እሱ ነፍሰ ገዳይ ነው። (ዮሐንስ 8:44) ከጦርነትና ከዓመፅ በስተ ጀርባ ያሉት ዋነኛ ጠንሳሾች ሰይጣንና ሌሎች ክፉ መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው።—ራእይ 12:9, 12

እኛ የጦርነትንና የዓመፅን ዋነኛ መንስኤዎች ማስወገድ አንችልም፤ አምላክ ግን ይችላል።

ሃይማኖት እና ጦርነት

ብዙውን ጊዜ ሃይማኖቶች ጦርነትን ይደግፋሉ፣ ያበረታታሉ ወይም ተቀባይነት እንዳለው ይናገራሉ። እነዚህ ሃይማኖቶች “ታላቂቱ ባቢሎን” የሚል የጋራ መጠሪያ ከተሰጣቸው የሐሰት ሃይማኖቶች መካከል ይመደባሉ። (ራእይ 18:2) አምላክ ታላቂቱ ባቢሎን ‘በምድር ላይ ለታረዱ ሰዎች ሁሉ ደም’ ተጠያቂ እንደሆነች ተናግሯል። (ራእይ 18:24) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “ታላቂቱ ባቢሎን ማን ናት?” የሚለውን ርዕስ jw.org ላይ አንብብ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ