የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 176
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ ምን ይላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ ምን ይላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ አስቀድሞ ተናግሯል?
  • አምላክ ሰዎችን በበሽታ የቀጣበት ጊዜ አለ?
  • በዛሬው ጊዜ ያሉት ወረርሽኞች አምላክ እየቀጣን እንዳለ ያሳያሉ?
  • ወረርሽኞች የሚወገዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
  • ስለ በሽታ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
  • አዲስ ዓለም ያስፈልገናል!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2021
  • 6 ሚሊዮን ሰዎች በኮቪድ ሕይወታቸውን አጥተዋል—መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ተናግሮ ይሆን?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ከዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወደፊት ምን ይከሰት ይሆን?
    ንቁ!—2005
  • ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት የሚኖርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 176
ምድር ላይ ወረርሽኝ ወደ ተለያዩ አህጉራት ሲሰራጭ የሚያሳይ ሥዕል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻዎቹ ቀናት ቸነፈር (ወረርሽኞችን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎች) እንደሚከሰት አስቀድሞ ተናግሯል። (ሉቃስ 21:11) እንዲህ ያሉት ወረርሽኞች አምላክ እየቀጣን እንዳለ የሚያሳዩ አይደሉም። እንዲያውም አምላክ በመንግሥቱ አማካኝነት ወረርሽኞችን ጨምሮ ሁሉንም የጤና ችግሮች በቅርቡ ያስወግዳል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ አስቀድሞ ተናግሯል?

  • አምላክ ሰዎችን በበሽታ የቀጣበት ጊዜ አለ?

  • በዛሬው ጊዜ ያሉት ወረርሽኞች አምላክ እየቀጣን እንዳለ ያሳያሉ?

  • ወረርሽኞች የሚወገዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

  • ስለ በሽታ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወረርሽኝ አስቀድሞ ተናግሯል?

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ኮቪድ-19፣ ኤድስ ወይም የኅዳር በሽታ ያሉ ወረርሽኞችን በስም ጠቅሶ ትንቢት አይናገርም። ሆኖም “ቸነፈር” እና “ገዳይ መቅሰፍት” እንደሚከሰት አስቀድሞ ተናግሯል። (ሉቃስ 21:11፤ ራእይ 6:8) እነዚህ ክንውኖች ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ወይም “የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት” ገጽታዎች ናቸው።—2 ጢሞቴዎስ 3:1፤ ማቴዎስ 24:3

አምላክ ሰዎችን በበሽታ የቀጣበት ጊዜ አለ?

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሰዎችን በበሽታ የቀጣባቸው ጊዜያት እንዳሉ ይገልጻል። ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎችን በሥጋ ደዌ ቀጥቷል። (ዘኁልቁ 12:1-16፤ 2 ነገሥት 5:20-27፤ 2 ዜና መዋዕል 26:16-21) ሆኖም በእነዚህ ጊዜያት ሰዎችን የቀጣው በጅምላ አልነበረም፤ ጥፋት ያልሠሩ ሰዎች በበሽታው አልተያዙም። ከዚህ ይልቅ አምላክ የቀጣው በእሱ ላይ ያመፁ ሰዎችን ለይቶ ነው።

በዛሬው ጊዜ ያሉት ወረርሽኞች አምላክ እየቀጣን እንዳለ ያሳያሉ?

አያሳዩም። አንዳንድ ሰዎች አምላክ በዛሬው ጊዜ ሰዎችን በወረርሽኞችና በሌሎች በሽታዎች እንደሚቀጣ ይናገራሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ሐሳብ አይደግፍም። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

አንደኛው ምክንያት ጥንትም ሆነ በዛሬው ጊዜ ያሉ አንዳንድ የአምላክ አገልጋዮች በበሽታ መያዛቸው ነው። ለምሳሌ ታማኝ የአምላክ አገልጋይ የሆነው ጢሞቴዎስ ‘በተደጋጋሚ የሚነሳ ሕመም’ ያሠቃየው ነበር። (1 ጢሞቴዎስ 5:23) ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው መታመሙ የአምላክን ሞገስ እንዳጣ የሚያሳይ እንደሆነ አይናገርም። በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ያሉ ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች ሊታመሙ ወይም በበሽታ ሊያዙ ይችላሉ። ይህ ማንም ሰው ሊያጋጥመው የሚችል ነገር ነው።—መክብብ 9:11

በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ክፉዎችን የሚቀጣበት ጊዜ ገና እንዳልደረሰ ይገልጻል። ከዚህ ይልቅ አሁን የምንኖረው ‘በመዳን ቀን’ ማለትም አምላክ ሰዎች ሁሉ ወደ እሱ እንዲቀርቡና እንዲድኑ ግብዣ እያቀረበ ባለበት ጊዜ ውስጥ ነው። (2 ቆሮንቶስ 6:2) አምላክ “የመንግሥቱ ምሥራች” በዓለም ዙሪያ እንዲሰበክ በማድረግ ይህን ግብዣ አቅርቧል።—ማቴዎስ 24:14

ወረርሽኞች የሚወገዱበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

አዎ። መጽሐፍ ቅዱስ ማንም ሰው የማይታመምበት ጊዜ በቅርቡ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል። አምላክ በመንግሥቱ አማካኝነት ሁሉንም በሽታዎች ያስወግዳል። (ኢሳይያስ 33:24፤ 35:5, 6) መከራ፣ ሥቃይና ሞትን ያስቀራል። (ራእይ 21:4) ከዚህም ሌላ ሰዎችን ከሞት በማስነሳት ገነት በሆነች ምድር ላይ ጥሩ ጤና አግኝተው እንዲኖሩ ያደርጋል።—መዝሙር 37:29፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15

ስለ በሽታ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ማቴዎስ 4:23፦ “[ኢየሱስ] በምኩራቦቻቸው እያስተማረና የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም በሕዝቡ መካከል ያለውን ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በመላዋ ገሊላ ተዘዋወረ።”

የሚያስተላልፈው መልእክት፦ ኢየሱስ የፈጸማቸው ተአምራት የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ለሰው ልጆች ሁሉ ምን እንደሚያደርግ በተወሰነ ደረጃ ያሳያሉ።

ሉቃስ 21:11፦ “ቸነፈር ይሆናል።”

የሚያስተላልፈው መልእክት፦ በስፋት የተሰራጩ የጤና ችግሮች የመጨረሻዎቹ ቀናት ምልክት ገጽታዎች ናቸው።

ራእይ 6:8፦ “እነሆ ግራጫ ፈረስ ነበር፤ በእሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበር። መቃብርም በቅርብ ይከተለው ነበር። ሞትና መቃብርም . . . በገዳይ መቅሰፍት . . . እንዲገድሉ . . . ሥልጣን ተሰጣቸው።”

የሚያስተላልፈው መልእክት፦ በራእይ መጽሐፍ ላይ የተጠቀሱትን አራት ፈረሰኞች አስመልክቶ የተነገረው ትንቢት ወረርሽኞች እኛ ባለንበት ዘመን እንደሚከሰቱ ይጠቁማል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ