የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 193
  • ዳንኤል ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ዳንኤል ማን ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳንኤል ምን ይነግረናል?
  • ዳንኤል—ክስ የቀረበበት መጽሐፍ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
  • የዳንኤል መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • የዳንኤል መጽሐፍና አንተ
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
  • ዓለምን የለወጡ አራት ቃላት
    የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል!
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 193
ነቢዩ ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላክ ሲጸልይ።

ዳንኤል ማን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ዳንኤል በሰባተኛውና በስድስተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. የኖረ ታዋቂ አይሁዳዊ ነቢይ ነው። አምላክ ለዳንኤል ሕልሞችን የመፍታት ችሎታ ሰጥቶታል፤ ወደፊት ስለሚፈጸሙ ክንውኖችም ራእይ አሳይቶታል። ከዚህም ሌላ በስሙ የተሰየመውን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ እንዲጽፍ በመንፈሱ መርቶታል።—ዳንኤል 1:17፤ 2:19

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳንኤል ምን ይነግረናል?

ዳንኤል ያደገው፣ የኢየሩሳሌም ከተማና የአይሁዳውያን ቤተ መቅደስ በሚገኙበት በይሁዳ ነው። በ617 ዓ.ዓ. የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ተቆጣጠራት፤ ከዚያም “በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።” (2 ነገሥት 24:15፤ ዳንኤል 1:1) በወቅቱ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እንደነበረ የሚገመተው ዳንኤልም በግዞት ከተወሰዱት አንዱ ነበር።

የንጉሡ ጠባቂዎች ዳንኤልንና ሌሎች ወጣቶችን ወደ ባቢሎን ቤተ መንግሥት ሲወስዷቸው።

ዳንኤልና የተወሰኑ ወጣት ወንዶች (ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን ጨምሮ) ለመንግሥት ሥራ ልዩ ሥልጠና እንዲያገኙ ወደ ባቢሎን ቤተ መንግሥት ተወሰዱ። ዳንኤልና ሦስቱ ጓደኞቹ ከእምነታቸው ጋር የሚጋጭ ነገር እንዲያደርጉ ጫና ቢደርስባቸውም ለአምላካቸው ለይሖዋ ታማኝ ሆነው ጸንተዋል። (ዳንኤል 1:3-8) እነዚህ ወጣቶች የሦስት ዓመት ሥልጠና ካገኙ በኋላ ንጉሥ ናቡከደነጾር በጥበባቸውና በችሎታቸው አድናቆት ቸሯቸዋል፤ እንዲያውም “በመላ ግዛቱ ካሉት አስማተኛ ካህናትና ጠንቋዮች ሁሉ አሥር እጅ [እንደሚበልጡ]” ተናግሯል። ከዚያም ዳንኤልንና ጓደኞቹን በቤተ መንግሥት ውስጥ እንዲያገለግሉ ሾማቸው።—ዳንኤል 1:18-20

ይህ ከሆነ ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ ዳንኤል ወደ ቤተ መንግሥቱ ተጠራ፤ በወቅቱ በ90ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሳይሆን አይቀርም። በጊዜው ባቢሎንን ይገዛ የነበረው ቤልሻዛር፣ በግድግዳው ላይ በእጅ የተጻፉትን ሚስጥራዊ ቃላት እንዲፈታ ዳንኤልን ጠየቀው። ዳንኤልም የጽሑፉን ትርጉም አምላክ ስለገለጠለት፣ ባቢሎን በሜዶ ፋርስ ድል እንደምትደረግ ተናገረ። በዚያው ሌሊት ባቢሎን ወደቀች።—ዳንኤል 5:1, 13-31

ዳንኤል በግድግዳ ላይ የሰፈረውን የእጅ ጽሑፍ ሲተረጉም።

በሜዶ ፋርስ የግዛት ዘመን ዳንኤል ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆኖ ተሾመ፤ ንጉሥ ዳርዮስ ከዚያም የበለጠ ሥልጣን ሊሰጠው ይፈልግ ነበር። (ዳንኤል 6:1-3) ቅናት ያደረባቸው ባለሥልጣናት ዳንኤል ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል ሴራ ጠነሰሱ፤ ሆኖም ይሖዋ አዳነው። (ዳንኤል 6:4-23) ዳንኤል ወደ ሕይወቱ ማብቂያ ሲቃረብ አንድ መልአክ ተገልጦለት ‘እጅግ የተወደደ ሰው’ መሆኑን ሁለት ጊዜ ነግሮታል።—ዳንኤል 10:11, 19

እነዚህ ክንውኖች ዳንኤል፦ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ እምነት ያሳየ ሰው በሚለው ባለ ሁለት ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ ድራማ ላይ ሕያው በሆነ መንገድ ቀርበዋል፤ ቪዲዮውን እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የዳንኤል መጽሐፍ—ታሪክ ምን ያሳያል?

ዳንኤል የዘገበው፦ ናቡከደነጾር ግዙፍ ምስል ካቆመ በኋላ ለምስሉ ተደፍተው እንዲሰግዱ ተገዢዎቹን አዘዘ፤ ይህን ያላደረጉትን ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ጣላቸው።—ዳንኤል 3:1-6

ታሪክ ምን ያሳያል? ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚገልጸው ናቡከደነጾር በባቢሎን አስገራሚ የግንባታ ፕሮጀክቶችን ያከናወነው “ለራሱ ዝና ለማትረፍ ብቻ ሳይሆን ለአማልክቱም ክብር ለማምጣት ነው። ‘ሕዝቡ ታላላቅ የሆኑትን አማልክት እንዲያመልኩ ያደረጋቸው’ እሱ መሆኑን ተናግሯል።”

ሰዎችን ወደ እቶን እሳት ከመጣል ጋር በተያያዘም በጥንታዊ የባቢሎን መዛግብት ውስጥ የተጠቀሱ መረጃዎች እናገኛለን፤ አንዳንዶቹ ዘገባዎች በንጉሡ ትእዛዝ ወደ እሳት የተጣሉ ሰዎች እንዳሉ ይገልጻሉ። በናቡከደነጾር ዘመን የተጻፈ አንድ ጥንታዊ ጽሑፍ የባቢሎንን አማልክት ያቃለሉ ባለሥልጣናት ስለተበየነባቸው ቅጣት ይናገራል። ጽሑፉ እንዲህ ይላል፦ “አጥፏቸው፣ አቃጥሏቸው፣ ለብልቧቸው፣ . . . ወደ ምድጃው ጣሏቸው . . . ጭሳቸው እየተትጎለገለ እንዲወጣ በሚንበለበለው እሳት አጋዩአቸው።”a

ዳንኤል የዘገበው፦ ንጉሥ ናቡከደነጾር ስላከናወናቸው የግንባታ ሥራዎች ጉራውን ነዝቷል።—ዳንኤል 4:29, 30

በባቢሎን በቁፋሮ የተገኘ ጡብ፤ የናቡከደነጾር ስም ተቀርጾበታል

ታሪክ ምን ያሳያል? “ራሱ ናቡከደነጾር ለቀጣዮቹ ትውልዶች ባሰፈረው መዝገብ ላይ . . . በጽድቁና በኃይሉ የሚተማመን ታላቅ ንጉሥ እንደሆነ ገልጿል።”b ለምሳሌ በአንድ ሕንፃ ላይ የተገኘው ጽሑፍ እንደሚያሳየው ናቡከደነጾር እንዲህ ብሏል፦ “እንደ ተራራ ሊገፋ የማይችል ታላቅ ግንብ በቅጥራንና በጡብ ሠርቻለሁ። . . . ስሜ ለዘላለም እንዲታወስ የኢሳጂላንና የባቢሎንን ምሽጎች አጠናክሬያለሁ።”c ከባቢሎን በቁፋሮ የወጡት አብዛኞቹ ጡቦች የናቡከደነጾር ስም ተቀርጾባቸዋል።

ዳንኤል የዘገበው፦ ንጉሥ ቤልሻዛር ዳንኤልን በመንግሥቱ ላይ “ሦስተኛ ገዢ” እንደሚያደርገው ቃል ገብቶለታል።—ዳንኤል 5:1, 13-16

በ550 ዓ.ዓ. የተጻፈው ይህ ጥንታዊ መዝገብ ስለ ናቦኒደስና ስለ ልጁ ስለ ቤልሻዛር ይናገራል

ታሪክ ምን ያሳያል? በዳንኤል ምዕራፍ 5 ላይ የተገለጹት ክንውኖች በተፈጸሙበት ወቅት ንጉሥ የነበረው ናቦኒደስ የተባለ ሰው ነው። ይሁንና ናቦኒደስ በአብዛኛው የግዛት ዘመኑ የኖረው በባቢሎን ሳይሆን በአረቢያ ነበር። ታዲያ እሱ ባልነበረበት ወቅት ባቢሎንን የሚያስተዳድረው ማን ነበር? ሬይመንድ ፊሊፕ ዶኸርቲ የተባሉት የታሪክ ምሁር ናቦኒደስ ኤንድ ቤልሻዛር የተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “[አንድ ጥንታዊ ጽሑፍ] እንደሚገልጸው ናቦኒደስ ንግሥናውን ለበኩር ልጁ ማለትም ለቤልሻዛር ሰጥቶት ነበር። ቤልሻዛር አባቱን ተክቶ መንግሥታዊ ሥራዎችን ያከናውን ነበር።” ናቦኒደስና ቤልሻዛር በመንግሥቱ ውስጥ አንደኛውንና ሁለተኛውን ቦታ ስለያዙ ቤልሻዛር ለዳንኤል ሊሰጠው ቃል የገባለት ሦስተኛውን ቦታ ነው።

a ጆርናል ኦቭ ባይብል ሊትረቸር፣ ጥራዝ 128 ቁጥር 2 ገጽ 279, 284

b ባቢሎን—ሲቲ ኦቭ ዎንደርስ፣ በኧርቪንግ ፊንክል እና ማይክል ሲሞር ገጽ 17

c አርኪኦሎጂ ኤንድ ዘ ባይብል በጆርጅ ባርተን ገጽ 479

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ