panitan/stock.adobe.com
ኢየሱስ ድህነትን ያስወግዳል
ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ለሰዎች ታላቅ ፍቅር አሳይቷል፤ በተለይ ለድሆችና ለተጨነቁ ሰዎች ልዩ ፍቅር ያሳይ ነበር። (ማቴዎስ 9:36) እንዲያውም ለሰዎች ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል። (ማቴዎስ 20:28፤ ዮሐንስ 15:13) በቅርቡ ደግሞ፣ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ያለውን ሥልጣን ተጠቅሞ ድህነትን ከመላው ምድር ያስወግዳል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ማራኪ ቃላትን በመጠቀም ኢየሱስ የሚያደርገውን ነገር ይገልጻል፦
“በሕዝቡ መካከል ላሉት ችግረኞች ጥብቅና ይቁም፤ የድሃውን ልጆች ያድን።”—መዝሙር 72:4
ኢየሱስ ላደረገልን ነገር እንዲሁም ወደፊት ለሚያደርግልን ነገር ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? አንዱ መንገድ ‘ስለ አምላክ መንግሥት ምሥራች’ መማር ነው፤ ኢየሱስ የሰበከው ስለዚህ መንግሥት ነበር። (ሉቃስ 4:43) “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።