alfa27/stock.adobe.com
ኢየሱስ ወንጀልን ያስወግዳል
ኢየሱስ የወንጀልና የግፍ ሰለባ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ በሚገባ ይረዳል። በሐሰት ተከሷል፤ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ተደብድቧል፤ ያለጥፋቱ ተፈርዶበታል እንዲሁም በሚያሠቃይ ሁኔታ ተገድሏል። ምንም ኃጢአት ባይሠራም ‘በብዙዎች ምትክ ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል።’ (ማቴዎስ 20:28፤ ዮሐንስ 15:13) አሁን የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ እየገዛ ሲሆን በቅርቡ ወንጀልን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማስወገድ በመላው ምድር ላይ ፍትሕ እንዲሰፍን ያደርጋል።—ኢሳይያስ 42:3
መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ዓለማችን ምን መልክ እንደሚኖራት ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦
“ክፉዎች አይኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤ እነሱ ግን በዚያ አይገኙም። የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል።”—መዝሙር 37:10, 11
ኢየሱስ ላደረገልን ነገር እንዲሁም ወደፊት ለሚያደርግልን ነገር ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? አንዱ መንገድ ‘ስለ አምላክ መንግሥት ምሥራች’ መማር ነው፤ ኢየሱስ የሰበከው ስለዚህ መንግሥት ነበር። (ሉቃስ 4:43) “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።