የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 68
  • ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • እውነት ሲኦል አለ? የመጽሐፍ ቅዱሱ ሲኦል ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ሰዎች ስለ ሲኦል ያላቸው እምነት ተለውጧልን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ሲኦል ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ሲኦል ምን ዓይነት ቦታ ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 68

ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሲኦል ወይም ሔድስ የሚያመለክቱት ሰዎች በእሳት የሚሠቃዩበትን ቦታ ሳይሆን የሰው ልጆችን መቃብር ነው። ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው? ጥሩ ሰዎችም ሆነ መጥፎ ሰዎች ሲኦል ይገባሉ። (ኢዮብ 14:13 የ1954 ትርጉም፤ መዝሙር 9:17) መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም የሰው ልጆች የሚገቡበት ይህ መቃብር “ለሕያዋን ሁሉ [የተመደበ] ስፍራ” እንደሆነ ይናገራል።​—ኢዮብ 30:23

ኢየሱስም እንኳ ሲሞት የሄደው ወደ ሲኦል ነው። ያም ሆኖ አምላክ ከሞት ስላስነሳው ‘በሲኦል አልቀረም።’​—የሐዋርያት ሥራ 2:31, 32 አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሲኦል ለዘላለም ይቀጥላል?

ሲኦል ውስጥ የገቡ ሰዎች ሁሉ ከሲኦል መውጣታቸው አይቀርም፤ ኢየሱስ ከአምላክ ያገኘውን ኃይል ተጠቅሞ ከሞት ያስነሳቸዋል። (ዮሐንስ 5:28, 29፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15) ራእይ 20:13 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ወደፊት የሚከናወነውን ትንሣኤ አስመልክቶ ሲናገር “ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ውስጥ የነበሩትን ሙታን ሰጡ” ይላል። ሲኦል በውስጡ ያለውን በሙሉ ከሰጠ በኋላ ይወገዳል፤ ከዚያ በኋላ ‘ሞት ስለማይኖር’ ማንም ሰው ሲኦል ውስጥ አይገባም።​—ራእይ 21:3, 4፤ 20:14

ይሁን እንጂ የሞቱ ሰዎች ሁሉ ሲኦል ይገባሉ ማለት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት ሠርተው ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ እንደማይሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ዕብራውያን 10:26, 27) እንዲህ ያሉ ሰዎች ሲሞቱ የሚገቡት ሲኦል ውስጥ ሳይሆን ገሃነም ውስጥ ነው፤ ገሃነም ዘላለማዊ ጥፋትን ያመለክታል። (ማቴዎስ 5:29, 30) ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩት አንዳንድ ግብዝ የሃይማኖት መሪዎች ወደ ገሃነም እንደሚገቡ ተናግሮ ነበር።​—ማቴዎስ 23:27-33

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ