የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • nwt ገጽ 1702-1703
  • ለ1 የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለ1 የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከ4026 ዓ.ዓ. በኋላ
  • 1943 ዓ.ዓ.
  • ከ1070 ዓ.ዓ. በኋላ
  • 29 ዓ.ም.
  • 33 ዓ.ም.
  • በ1914 ዓ.ም. ገደማ
  • ወደፊት
  • ሁላችንንም የሚመለከት ጥንታዊ ትንቢት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • ይሖዋ ዓላማውን ይገልጣል
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
  • የእባቡ ዘር፣ እንዴት ተጋለጠ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ስምምነት
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
ለተጨማሪ መረጃ
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ለ1 የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት

ለ1

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት

በወረቀት የሚታተመው

ይሖዋ አምላክ የመግዛት መብት አለው። የእሱ አገዛዝ ከሁሉ የተሻለ ነው። ለምድርና ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ ፍጻሜውን ያገኛል።

አዳምና ሔዋን እባብ በአቅራቢያቸው ሆኖ በኤደን ገነት ውስጥ

ከ4026 ዓ.ዓ. በኋላ

‘እባቡ’ በይሖዋ የመግዛት መብትና አገዛዝ ላይ ጥያቄ አስነሳ። ይሖዋም የእባቡን ይኸውም የሰይጣንን ራስ የሚጨፈልቅ “ዘር” እንደሚያስነሳ ቃል ገባ። (ዘፍጥረት 3:1-5, 15) ሆኖም ይሖዋ ለተወሰነ ጊዜ ሰዎች በሰይጣን ተጽዕኖ ሥር ሆነው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፈቀደ።

አብርሃም አምላክ ቃል የገባውን ተስፋ ሲሰማ

1943 ዓ.ዓ.

ይሖዋ ለአብርሃም ተስፋ የተደረገበት ዘር በእሱ የዘር ሐረግ በኩል እንደሚመጣ ነገረው።–⁠ዘፍጥረት 22:18

ንጉሥ ዳዊት

ከ1070 ዓ.ዓ. በኋላ

ይሖዋ ለንጉሥ ዳዊት፣ ቆየት ብሎ ደግሞ ለልጁ ለሰለሞን ተስፋ የተደረገበት “ዘር” በእነሱ የዘር ሐረግ በኩል እንደሚመጣ አረጋገጠላቸው።–⁠2 ሳሙኤል 7:12, 16፤ 1 ነገሥት 9:3-5፤ ኢሳይያስ 9:6, 7

ኢየሱስ ሲጠመቅ

29 ዓ.ም.

ይሖዋ፣ የዳዊትን ዙፋን የሚወርሰው ተስፋ የተደረገበት “ዘር” ኢየሱስ መሆኑን አስታወቀ።–⁠ገላትያ 3:16፤ ሉቃስ 1:31-33፤ 3:21, 22

ኢየሱስ ሲሞት

33 ዓ.ም.

እባቡ ይኸውም ሰይጣን፣ ኢየሱስን በማስገደል ተስፋ የተሰጠበትን “ዘር” ተረከዝ አቁስሏል። ይሁንና ይሖዋ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት በሰማይ ሕይወት የሰጠው ከመሆኑም ሌላ ፍጹም ሕይወቱን መሥዋዕት በማድረግ የከፈለውን ዋጋ ተቀብሎታል፤ ይህም የአዳምን ዘሮች ኃጢአት ይቅር ለማለትና ለእነሱ የዘላለም ሕይወት ለመስጠት መሠረት ሆኖ ያገለግላል።–⁠ዘፍጥረት 3:15፤ የሐዋርያት ሥራ 2:32-36፤ 1 ቆሮንቶስ 15:21, 22

እባቡ ሰይጣን በራእይ መጽሐፍ እንደተገለጸው ወደ ምድር ሲወረወር

በ1914 ዓ.ም. ገደማ

ኢየሱስ እባቡን ይኸውም ሰይጣንን ወደ ምድር በመወርወር እንቅስቃሴው በምድር ላይ ብቻ እንዲወሰን አድርጓል።–⁠ራእይ 12:7-9, 12

ኢየሱስ በራእይ መጽሐፍ ተስፋ እንደተገባው በሰማይ በዙፋኑ ላይ ሆኖ ምድርን ሲገዛ

ወደፊት

ኢየሱስ ሰይጣንን ለ1,000 ዓመት ካሰረው በኋላ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያጠፋዋል፤ በምሳሌያዊ አነጋገር ራሱን ይጨፈልቀዋል። ይሖዋ ለምድርም ሆነ ለሰው ልጆች ያወጣው የመጀመሪያ ዓላማ ፍጻሜውን ያገኛል፤ ስሙ ከነቀፋ ነፃ ይሆናል፤ እንዲሁም የአገዛዙ ትክክለኝነት ይረጋገጣል።–⁠ራእይ 20:1-3, 10፤ 21:3, 4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ