ጽንፈ ዓለም—በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይስ በፍጥረት?
ጽንፈ ዓለም በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይስ በፍጥረት በሚለው እልባት ያላገኘ ክርክር ረገድ በታላቋ ብሪታንያ፣ በኒው ካስል ዩኒቨርስቲ የንድፈ ሐሳባዊ ፊዝክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፖል ዴቪስ ጎድ ኤንድ ዘ ኒው ፊዝክስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ የሰጡት የሚከተለው ሐሳብ በእጅጉ ትኩረት የሚስብ ነው።
“ጽንፈ ዓለም ድንገት የተገኘ ነገር ቢሆን ይህ ነው የሚባል ሥርዓት ያለው አካል የመሆኑ ዕድል እጅግ በጣም የመነመነ ነው። . . . ሥርዓት ያለው መሆኑን በግልጽ ለመመልከት የሚቻል በመሆኑ ግን ጽንፈ ዓለም የሚገኝበት ሁኔታ በጣም ከፍተኛ ብዛት ካላቸው አማራጮች መካከል በጥንቃቄ ‘የተመረጠ’ ነው ከሚለው ድምዳሜ ልንሸሽ የምንችል አይመስልም። ከግምት ውስጥ ሊገቡ ከማይችሉ ጥቂት ነገሮች በስተቀር በአብዛኛው ሁሉም በሥርዓት የሚመሩ ናቸው። ይህ ለመገመት እንኳን አዳጋች የሆነው የመጀመሪያ ሁኔታ በምርጫ የተጀመረ ከሆነ ይህን ሁኔታ የመረጠ መራጭ ወይም ንድፍ አውጭ መኖር አለበት።
በእውነትም፣ አንድ ሕንጻ ሠሪ ለዓላማው የሚያገለግለውን ሕንጻ ፕላን እንደሚያወጣና ለግንባታ የሚያገለግሉትን ዕቃዎች እንደሚመርጥ ሁሉ ስሙ ይሖዋ የሆነው ሁሉን የሚችል አምላክ ደግሞ ጽንፈ ዓለሙን ፈጥሯል። (መዝሙር 83:18 አዓት፤ ራእይ 4:11) በእርግጥም የፕሮፌሰር ዴቪስ ድምዳሜ በዕብራውያን 3:4 [በ1980 ትርጉም ] ላይ የሚገኘውን የሐዋርያው ጳውሎስ ቃላት ያስታውሰናል። “ሁሉን የሠራ . . . እግዚአብሔር ነው።”
[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ምንጭ]
NASA photos