የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 1/8 ገጽ 32
  • ግራጫው ፈረስ ግልቢያውን ቀጥሏል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ግራጫው ፈረስ ግልቢያውን ቀጥሏል
  • ንቁ!—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኤድስ የያዛቸውን ሰዎች መርዳት
    ንቁ!—1995
  • ለኤድስ ተጋልጫለሁን?
    ንቁ!—1994
  • ደምን በደም ሥር መውሰድ—ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
    ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?
  • ከኤድስ ራሴን መጠበቅ የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—1993
ንቁ!—1994
g94 1/8 ገጽ 32

ግራጫው ፈረስ ግልቢያውን ቀጥሏል

ነቢዩ ዮሐንስ በአምላክ መንፈስ ተነድቶ ቸነፈር ልክ ሞት እንደሚጋልበው ግራጫ ፈረስ ምድርን በሙሉ የሚያዳርስበት ጊዜ እንደሚመጣ ተንብዮ ነበር። (ራእይ 6:​8 የ1980 ትርጉም ) የኤድስ በአስደንጋጭ ሁኔታ መዛመት በዚህ ዘመን የምንኖር መሆናችንን የሚያስገነዝበን አሳዛኝ ማስረጃ ሆኗል። እንዲያውም የኒው ዮርክ ከተማ የጤና አጠባበቅ ባለ ሥልጣኖች የኤድስን ከፍተኛ ዕድገት “መጪው መቅሰፍት” ሲሉ ጠርተው⁠ታል።

በታይላንድ አገር በአሁኑ ጊዜ ከ73ቱ ክፍላተ ሀገራት መካከል በ70ዎቹ ውስጥ ኤድስ ተዛምቷል። በ1987 በባንኮክ ከሚገኙት አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎች መካከል በኤድስ የተለከፉት 1 በመቶ የሚያክሉት ብቻ ነበሩ። በ1989 አጋማሽ ላይ ግን ከ40 በመቶ የሚበልጡ ተለክፈው ነበር። ብራዚል በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተመርምረው ኤድስ እንደያዛቸው የሚረጋገጥባቸው ሰዎች 75,000 እንደሚደርስና ሌሎች 1.5 ሚልዮን የሚያክሉ ደግሞ በበሽታው እንደሚያዙ ገምታለች። በብራዚል ከሚገኙት 1,200 የሚያክሉ የደም ባንኮች መካከል በ1988 ባከማቹት ደም ላይ የኤድስ ምርመራ ያደረጉት 20 በመቶ የሚያክሉት ብቻ ነበሩ። በኤድስ ከተለከፉት ሰዎች መካከል 14 በመቶ የሚያክሉት በሽታው የተጋባባቸው በበሽታው ከተበከለ ደም ነው። በሪዮ ዲ ጃኔይሮ እና ሳኦ ፓውሎ የደም አለመርጋት በሽታ ካለባቸው በሽተኞች መካከል 75 በመቶ የሚያክሉት በኤድስ ተይዘዋል። በኮት ዲቩዋር 10 ከመቶ የሚያክሉ ነፍሰ ጡሮችና 10 ከመቶ የሚያክሉ ደም ለጋሾች በኤድስ የተለከፉ ናቸው።

አንድ አሜሪካዊ የጤና ጥበቃ ባለ ሥልጣን 87 ብሔራት በተካፈሉበት የኤድስ ስብሰባ ላይ “የኤች አይ ቪ (የኤድስ ቫይረስ) ወረርሽኝ በዩናይትድ ስቴትስና በዓለም ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል እስከ 1998 ድረስ አንድ ሚልዮን የሚያክሉ አሜሪካውያን የኤድስ በሽታ ሙሉ ምልክቶች የሚታይባቸው ሕሙማን እንደሚሆኑና ከዚህ ቁጥር በጣም የሚበልጡት ደግሞ የቫይረሱ ተሸካሚዎች እንደሚሆኑ ገምቷል። በቅርቡ ደግሞ የቫይረሱ ተሸካሚዎች ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ እጅግ እንደሚጨምር ተገምቷል። በኒው ዮርክ ከተማ በአሁኑ ጊዜ ኤድስ ከልብ በሽታና ከካንሰር ቀጥሎ ሦስተኛው ዋነኛ የሞት ምክንያት ሆኗል።

የደም ባንኮች በኤድስ የተበከለ ደም ለበሽተኞች በመስጠታቸው ምክንያት ተከሰዋል። ብዙዎቹም የጉዳት ካሣ እንዲከፍሉ ተበይኖባቸዋል። ወደፊትም ተጨማሪ ብዙ ክሶች ሊመሠረቱባቸው ይችላሉ። የአሜሪካ የደም ባንኮች ማኅበር ዋና የሕግ አማካሪ “የወደፊቱ ጊዜ ምን ያመጣ ይሆን? እንጃ። የደም ማዕከሎች ከሕልውና ውጭ ሲሆኑ ይታየኛል” በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።

በእውነትም በቅርቡ የደም ባንኮች በሙሉ ከሕልውና ውጭ ይሆናሉ። ምክንያቱም ኤድስ፣ ሆስፒታል፣ በሽታ ወይም ሞት የማይኖርበት ዓለም የምናይበት ጊዜ ቀርቧል። ስለ ግራጫው ፈረስ ግልቢያ የገለጸልን ዮሐንስ “አዲስ ምድር” ማለትም የበሽታ ቸነፈር የማይነካው ሰብዓዊ ማኅበረሰብ እንደሚመሠረት አምላክ የሰጠውን ቃል መዝግቦልናል። (ራእይ 21:​1–4) ይህ እስከሚሆን ድረስ ግን ግራጫው ፈረስ ግልቢያውን ስለማያቆም በአስቸኳይ ስለዚህ ተስፋ በቂ ግንዛቤ ማግኘት ይኖርብናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ