የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g93 4/8 ገጽ 3
  • ሞት ዓለም አቀፋዊው መቅሠፍት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሞት ዓለም አቀፋዊው መቅሠፍት
  • ንቁ!—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ረዥም ዕድሜ ለመኖር ያለን ተስፋ ምንድን ነው?
    ንቁ!—1997
  • ሞትን የምንፈራው ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2007
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?
    እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው?
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—1993
g93 4/8 ገጽ 3

ሞት ዓለም አቀፋዊው መቅሠፍት

በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ 50 ሚልዮን የሚያክሉ ሰዎች ይሞታሉ። በሌላ አነጋገር ይህ ማለት በቀን 137,000፣ በሰዓት 5,700፣ በአንድ ደቂቃ ወደ 100 የሚጠጉ ወይም በየሁለት ሴኮንዱ ከ3 ሰዎች በላይ ይሞታሉ ማለት ነው። የሞት መቅሠፍት የማያጠቃው አንድም ቤተሰብ የለም። ንጉሥም ሆነ ተራ ሰው፣ ሀብታምም ሆነ ድሀ፣ ወንድም ሆነ ሴት ሁሉም ከሞት አያመልጡም።

ዝነኛው አሜሪካዊ አሳታሚ፣ የፈጠራ ሰውና ዲፕሎማት የሆኑት ቤንጃሚን ፍራንክሊን በ1789 ለአንድ ወዳጃቸው “በዚህ ዓለም ላይ ከሞትና ከግብር ነፃ የሆነ ሰው የለም” በማለት ጽፈዋል። ይሁን እንጂ ይህ ግንዛቤያቸው አዲስ ነገር አይደለም። 2,800 ከሚያህሉ ዓመታት በፊት የጥንቱ የእስራኤል ሕዝብ ንጉሥ የነበረው ጠቢቡ ሰሎሞን “ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና” ሲል ገልጾ ነበር። እሱም ቢሆን ከላይ ያለውን ሲናገር 3,000 ከሚያህሉ ዓመታት በፊት በምድር ላይ ለነበረው ለመጀመሪያው ሰው “አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም ትመለሳለህና” ተብሎ የተነገረውን እውነት ማጠናከሩ ነበር። — መክብብ 9:5፤ ዘፍጥረት 3:19

ሞት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ያለ ነገር ሆኖ ቢቆይም አሁንም የከፍተኛ ሐዘን ምንጭ መሆኑ አልቀረም። በተፈጥሯችን የምንፈልገው መሞትን ሳይሆን በሕይወት መኖርን ነው ቢባል ትክክል ነው። ከቤተሰባችንና ከወዳጆቻችን ጋር ያለን ጠንካራ ትስስር እንዳለ እንዲቀጥል እንሻለን። ነገር ግን ዓመታት ባለፉ ቁጥር እነዚህ የአንድነት ማሰሪያዎች አንድ በአንድ በሞት ይበጠሳሉ። አያቶቻችን፣ ወላጆቻችን እንዲሁም ወዳጆቻችን ይሞታሉ።

“መቶና ከዚያም በላይ ዕድሜ የሚኖሩ ሰዎች ከ113 ዓመት የማለፋቸው አጋጣሚ በጣም የመነመነ መሆኑ የማይታበል ሀቅ ነው። በአሁኑ ጊዜ ያለው የተወሰነ የዕድሜ ጣራ ማንኛውም ሰው ከ120 ዓመቴም በኋላ የልደት ቀኔን አከብራለሁ የሚል እምነት እንዳያድርበት ያግደዋል” በማለት ዘ ጊነስ ቡክ ኦቭ ወርልድ ሪኮርድስ የተባለው መጽሐፍ ይገልጻል። በ19ኛው መቶ ዘመን ከተከናወኑት ከእነዚህ ነገሮች በፊት የነበሩትን ታሪካዊ ክንዋኔዎች ሳንጨምር ዊንስተን ቸርችል (1874) ወይም ሞሃንዳስ ጋንዲ (1869) በተወለዱበት ዘመን የነበረ፣ በ1867 ሩስያ አላስካን ለዩናይትድ ስቴትስ ስትሸጥ በሕይወት የነበረ አለዚያም ደግሞ በ1865 አብርሃም ሊንከን ሲገደሉ በሕይወት የነበረና ይህንኑ መተረክ የሚችል አንድም ሰው በአሁኑ ጊዜ በሕይወት አይገኝም።

በዘመናዊ ሕክምናና በሳይንስ ረገድ ፈጣን እድገት ቢደረግም የሰው ልጅ የሕይወት ዘመን ግን በጥንት ዘመን ይኖር የነበረው ሙሴ ከተናገረው የዕድሜ ጣራ እልፍ ማለት አልቻለም:- “ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እርሱም በመከራና በሐዘን የተሞላ ነው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።” (መዝሙር 90:10 የ1980 ትርጉም ) ይህ አጠቃላይ የሆነ አገላለጽ ነው። ሙሴ ራሱ 120 ዓመት ኖሯል።

ሕይወት በመከራ የተሞላ ሆኖ የወዳጅና የዘመድ ሞት ልዩ ሥቃይና ሐዘን ያስከትላል። ብዙውን ጊዜ ዘመዳቸው በሞት የተለያቸው ሰዎች የጤና ቀውስ ይደርስባቸዋል፤ አልፎ ተርፎም ሊታመሙና ሊሞቱ ይችላሉ። የትኛውም የቤተሰብ አባል ቢሞት የባዶነት ስሜት መፍጠሩ አይቀርም። አንድ የሥነ–አእምሮ ሊቅ “ወላጅህ ሲሞት የቀድሞ ትዝታዎችህን ታጣለህ። ልጅህ ሲሞት ተስፋህ ባዶ ይሆናል” በማለት ገልጸውታል። ከዚያ ተከትሎ የሚመጣውን ጭንቀትና የስሜት መረበሽ በቃላት መግለጽ ሊያዳግት ይችላል። ብዙውን ጊዜ ገንዘብ ነክ ጥሪቶች ይሟጠጣሉ፤ ይህም ችግሩን ይበልጥ ያወሳስበዋል። አንዳንድ የቀብር ሥርዓት ልማዶችና ወጎች እንዲጠበቁ የሚደረገው ግፊት ሐዘኑን ሊያከብደው ይችላል።

ታዲያ የምናፈቅረው ሰው ሲሞት ከሚደርሱብን ጫናዎችና ጭንቀቶች መካከል አንዳንዶቹን ማቃለል የምንችልበት መንገድ ይኖር ይሆን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ