የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g94 10/8 ገጽ 21
  • ብልህ መሀንዲሶች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብልህ መሀንዲሶች
  • ንቁ!—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የምስጥ ኩይሳ
    ንቁ!—2008
  • ማሊ የተባሉት ወፎች ጎጆ
    ንድፍ አውጪ አለው?
ንቁ!—1994
g94 10/8 ገጽ 21

ብልህ መሀንዲሶች

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የንቁ! መጽሔት ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

በዚህ ገጽ ላይ በሥዕል እንደተገለጹት ያሉ ተፈጥሮያዊ ሕንፃዎችን አይተህ ታውቃለህን? በአፍሪካ የግጦሽ መስኮች የምስጥ ኩይሳዎች በብዛት ይታያሉ። አንዳንዶቹ ጠባብ ጭስ ማውጫ መሰል ቅርጽ ያላቸው ሲሆን አንዳንዴ ከ6 ሜትር በላይ ከፍታ አላቸው። ሌሎቹ እንደ አንበሳ ላሉ እንስሳ በሎች ከሩቅ አሻግሮ ለመመልከት የሚያመቹ በምድር ላይ ያሉ ትልቅ ጉልላቶች ናቸው።

በእያንዳንዱ ኩይሳ ውስጠኛ ክፍል ውስጥ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ትናንሽ ምስጦች ያሉባቸው አያሌ መተላለፊያዎችና አዳራሾች አሉ። አንዳንድ ምስጦች የራሳቸውን የፈንገስ የአትክልት ቦታዎች ይንከባከባሉ፤ በድርቅ ወራትም እንኳን በደንብ ያጠጧቸዋል። ይህ እንዴት ይቻላል? ከባድ ድርቅ የደቡብ አፍሪካን አንዳንድ ክፍሎች በመታበት በ1930ዎቹ ዓመታት የሥነ ተፈጥሮ ጠበብት የሆኑት ዶክተር ኢገን ማሪስ ምስጦች በሁለት ረድፎች ተከፍለው አንዱ ወገን ወደታች ሌላው ወገን ደግሞ በመተላለፊያዎቹ ውስጥ ወደላይ ሲወጣ አይተዋል። እነዚህ አነስተኛ ፍጥረቶች ሠላሳ ሜትር ያህል ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ቆፍረዋል! አንድ ምንጭ አግኝተዋል። ምስጦች በድርቅ ወቅት የፈንጊ ተክሎቻቸውን እንዴት እንደሚያጠጡ ማሪስ በዚህ መንገድ ደርሰውበታል።

ሚካኤል ሜይን ካልሃሪ በተባለው መጽሐፋቸው ስለ አንድ የምስጥ ኩይሳ ሲገልጹ “በምድር ላይ በሚኖር በየትኛውም እንስሳ ከተሠራው ጎጆ ሁሉ እጅግ የመጠቀ እንደሆነ ይታመናል። . . . ለሁሉም ማለትም ለፈንገሶቹም ሆነ ለምስጦቹ የሚስማማውን 100 እጅ እርጥበትና በ29 እና በ31 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መካካል ያለ ሙቀት ለማግኘትና ለመጠበቅ ይፈልጋሉ። . . . በውጤቱም እያንዳንዱ ጎጆ በቂ አየር ያገኛል።”

አሁን እነዚህ ጎጆዎች እንዴት አንደሚሠሩ ተመልከት። ምስጦቹ እያንዳንዱን ጥቃቅን አሸዋ ያለሰልሱና ከሌለው ጋር ያጣብቁታል። አንድ ኩይሳ ለመሥራት ምን ያህል ሚልዮን የአሸዋ ቅንጣቶች እንደሚያስፈልጉ ገምት! “ሰው በዚህ ምድር ላይ የገነባቸው ግዙፍ ሕንፃዎች የግብፅን ፒራሚዶች፣ የለንደኑን በመሬት ውስጥ ለውስጥ የሚሄድ የባቡር መስመር፣ የኒው ዮርክ ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎችን . . .፣ ከምስጥ ሥራ ጋር ማወዳደር፣ . . . የፍልፈል ቁልሎችን ከተራራዎች ጋር እንደማወዳደር ነው” ሲሉ ማሪስ ዘ ሶል ኦቭ ዘ ዋይት አንት (የነጭ ጉንዳን ሕይወት) በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ጽፈዋል። አክለውም “መጠንን ግምት ውስጥ ስናስገባ የሰው ሥራ 12 ሜትር ቁመት ካለው የምስጥ ኩይሳ ጋር እንዲተካከል ከተፈለገ ሰው ማተርሆርንን [ጫፉ 4, 300 ሜትር ከፍታ ያለው በሲውዘርላንድ የሚገኝ ተራራ] የሚያህል ከፍታ ያለው ሕንፃ መገንባት አለበት።”

ይሁን እንጂ ምስጦች ለሰው የሚሰጡት ጠቀሜታ ምንድን ነው? አንዱ ምስጦች የደረቁ ዕፅዋቶችን ስለሚመገቡ ቆሻሻ ያስወግዳሉ። “ደረቅ ነገሮችን ወደ መሬት ውስጥ በማስገባት የእሳት አደጋ እንዲቀነስ ከማድረጋቸውም በላይ በመሬት ውስጥ ያለውን አፈር ያዳብራሉ” ሲል በክሩገር ብሔራዊ መናፈሻ አንድ ሠሌዳ ላይ የሰፈረው ሐሳብ ይገልጻል።

ምናልባት አንተም እነዚህ አነስተኛ ምስጦች ብልህ መሀንዲሶች ለመባል እንደሚበቁ ትስማማ ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ