ስፍር ቁጥር የሌላቸውና ልዩ ልዩ ሕያዋን ነገሮች በምድር ላይ ሊኖሩ የቻሉት እንዴት ነው?
ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ በስም ከሚያውቋቸው 1.5 ሚልዮን የእንስሳት ዝርያዎች መካከል አንድ ሚልዮን የሚያክሉት ሦስት አፅቄዎች (insects) ናቸው። የምናውቃቸውን የሦስት አፅቄ ዓይነቶች በሙሉ ይመዝገቡ ቢባል 6,000 ገጾች ያሉት ኢንሳይክለፒዲያ ያስፈልጋል! እነዚህ ፍጥረታት የተገኙት እንዴት ነው? ዓይነታቸው ይህን ያህል ስፍር ቁጥር የሌለው የሆነውስ ለምንድን ነው? ተፈጥሮ ሚልዮን ጊዜ “ባለ ዕድል” ስለሆነች እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነገር ነው ወይስ በዓላማ የተዘጋጀ?
እስቲ በመጀመሪያ በፕላኔታችን ላይ ከሚገኙት የተለያዩ ሕያዋን ነገሮች አንዳንዶቹን በአጭሩ እንመልከት።
አስገራሚ አእዋፍ
አስደናቂ የሆነ ሥነ ተፈጥሮ ስላላቸው 9,000 የሚያክሉ የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች ምን ማለት ይቻላል? ሃሚንግ በርድ ከሚባሉት የወፍ ዝርያዎች አንዳንዶቹ መጠናቸው ከንብ ከፍ የሚለው በትንሹ ብቻ ነው። ይሁንና የበረራ ችሎታቸውና ቅልጥፍናቸው እጅግ ዘመናዊ የሆነ ሄሊኮፕተር ያስንቃል። እንደ አርክቲክ ተርን ያሉት ሌሎች የአእዋፍ ዝርያዎች ደግሞ በየዓመቱ ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው የሚሰደዱ ሲሆን ይህች ወፍ በእያንዳንዱ የደርሶ መልስ ጉዞ እስከ 35,000 ኪሎ ሜትር ድረስ ትበርራለች። ኮምፒዩተር ወይም አቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያ ባይኖራትም አቅጣጫዋን ሳትስት የፈለገችበት ቦታ ትደርሳለች። ይህ በተፈጥሮ ውርስ የሚተላለፍ ችሎታ እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይስ በዓላማ?
አስገራሚ ዕፅዋት
በተጨማሪም በዕፅዋት ዓለም ውስጥ የሚታይ እጅግ በጣም ብዙ የዓይነት ልዩነትና ውበት አለ። ከ350,000 በላይ የዕፅዋት ዝርያዎች አሉ። ከእነዚህ መካከል በግምት 250,000 የሚያክሉት የሚያብቡ ናቸው! በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ነገሮች በሙሉ በግዙፍነቱ አንደኛ የሆነው የሴኮያ ዛፍ ነው።
በራስህ የአትክልት ስፍራ ውስጥ ወይም በምትኖርበት አካባቢ ምን ያህል የተለያዩ አበባዎች ይበቅላሉ? በጣም ትንሽ ከሆነችውና በበረሃ አካባቢ ከምትበቅለው ዴዚ የምትባል አበባ ወይም ከባተርካፕ አንስቶ እስከ ኦርኪድ ድረስ የተለያየ አስገራሚ ኅብር ያላቸው እነዚህ አበባዎች የተላበሱት ውበትና ቅርጽ በጣም አስደናቂ ነው። አሁንም ‘እነዚህ ነገሮች እንዴት ሊገኙ ቻሉ በአጋጣሚ ወይስ በዓላማ?’ የሚል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።
ሕያዋን ነገሮች የሚርመሰመሱባቸው ውቅያኖሶች
በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ወንዞች፣ ሐይቆችና ውቅያኖሶች ውስጥ ስለሚገኘው ሕይወትስ ምን ማለት ይቻላል? ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ጨው አልባ በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እስከ 8,400 የሚደርሱ የዓሣ ዝርያዎች ሲኖሩ በውቅያኖሶች ውስጥ ያለው የዓሣ ዝርያ ቁጥር ደግሞ 13,300 ይደርሳል። ከእነዚህ ሁሉ በጣም ትንሽ የሆነችው ዓሣ በሕንድ ውቂያኖስ ውስጥ የምትገኘው ጎቢ የተባለችው ዝርያ ነች። ርዝማኔዋ አንድ ሴንቲ ሜትር ብቻ ነው። በጣም ትልቁ ዌል ሻርክ ደግሞ ቁመቱ እስከ 18 ሜትር ይደርሳል። ይህ አኃዝ ኢደንደሴ የሆኑትን (አከርካሪ የሌላቸውን) ወይም ደግሞ ገና እስካሁን ያልታወቁትን ዝርያዎች አይጨምርም!
ዕጹብ ድንቅ የሆነው አንጎል
ከሁሉ ይበልጥ አስገራሚ የሆነው ደግሞ የሰው አንጎል ነው። አንጎል ቢያንስ አሥር ቢልዮን ሕዋሰ ነርቮች (neurons) ያሉት ሲሆን እነዚህ እያንዳንዳቸው ከ1,000 የሚበልጡ ጋጥሚያ ሕዋሳተ ነርቭ (synapses) ወይም ከሌሎች የነርቭ ሴሎች ጋር ግንኙነት የሚያደርጉባቸው መጋጠሚያዎች አሏቸው። ኒውሮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ሪቻርድ ሬስተክ እንዲህ ብለዋል:- “በጣም ሰፊ በሆነው የአንጎል ሕዋሳተ ነርቭ ሥርዓት ውስጥ ያሉት መጣመሪያ ነጥቦች ጠቅላላ ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው።” (ዘ ብሬይን) በተጨማሪም “በአንጎል ውስጥ ከአሥር ትሪሊዮን እስከ አንድ መቶ ትሪሊዮን የሚደርሱ ጋጥሚያ ሕዋሳተ ነርቮች ሊኖሩ ይችላሉ” ብለዋል። ከዚያም የሚከተለውን አግባብነት ያለው ጥያቄ አንስተዋል:- “ከአሥር ቢልዮን እስከ መቶ ቢልዮን የሚደርሱ ሕዋሳት ያሉት እንደ አንጎል ያለ አካል ከአንዲት ሕዋስ ማለትም ከአንዲት እንቁላል እንዴት ሊገኝ ይችላል?” አንጎል የማንም ሌላ ወገን እርዳታ ሳያስፈልገው እንዲሁ በነሲባዊ ሂደት የተገኘ የአካል ክፍል ነው ወይስ የማሰብ ችሎታ ባለው አንድ አካል ንድፍ ወጥቶለት የተሠራ?
አዎን፣ የተለያየ ዓይነትና ንድፍ ያላቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕያዋን ነገሮች ሊገኙ የቻሉት እንዴት ነው? የተማርከው ይህ ሁሉ የተገኘው አጋጣሚዎች፣ ጭፍን የአዝጋሚ ለውጥ ሎተሪ ወይም ዕድል ባስገኘው ለውጥ ምክንያት እንደሆነ ነውን? ከሆነ አንዳንድ ሳይንቲስቶች የስነ ሕይወት ሳይንስ መሠረት ነው ስለተባለው ስለ አዝጋሚ ለውጥ ንድፈ ሐሳብ በፍጹም ቅንነት ያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመመልከት እንድትችል ማንበብህን ቀጥል።
[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
አንድ ቀላል የሆነ ካሜራ ሠሪ ካስፈለገው ከዚያ ይበልጥ እጅግ ውስብስብ የሆነው የሰው ዓይንስ?
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
አይን ውሃ
ብሌን
ብራንፊ (Cornea)
ሌንስ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
ማዘገቢያ (Iris)
ሌንስ ስጋ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
•••••••
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
የሌንስ አካባቢ
(ጎልቶ ሲታይ)
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
የሙሉ ዓይን ምስል
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
ነርቭ እይታ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
•••••••••••••••
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
ዝልግልግ ፈሳሽ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
እይታ ድራብ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
••••
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
መሂል ድራብ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
••••••••
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
ነጭ ድራብ
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሥዕል4]
•••••••