የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g01 5/8 ገጽ 3
  • እስር ቤቶች ከባድ ቀውስ ገጥሟቸዋል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እስር ቤቶች ከባድ ቀውስ ገጥሟቸዋል
  • ንቁ!—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መፍትሔ ይሆናል የተባለው ነገር ራሱ የችግሩ አካል ይሆን?
    ንቁ!—2001
  • ወንጀልን ማስቀረት ይቻል ይሆን?
    ንቁ!—2008
  • “እስረኞች ለውጥ እንዲያደርጉ መርዳት ይቻላልን?”
    ንቁ!—2005
  • በእርግጥ ለውጥ እንዲያደርጉ መርዳት ይቻል ይሆን?
    ንቁ!—2001
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2001
g01 5/8 ገጽ 3

እስር ቤቶች ከባድ ቀውስ ገጥሟቸዋል

“ወንጀልን ለመከላከል ተጨማሪ እስር ቤቶች መገንባት አንድን ቀሳፊ በሽታ ለማስወገድ ተጨማሪ መካነ መቃብሮች ከመገንባት ተለይቶ አይታይም።”​—⁠ሮበርት ጋንጂ፣ የፀባይ እርማት ኤክስፐርት

የሰዎችን ሞራል ላለመንካት ሲባል መጥፎውን እውነታ የመደበቅ ዝንባሌ በተስፋፋበት በዛሬው ዓለም “እስር ቤት” የሚለውን ደስ የማይል ቃል ለስለስ ባሉ ሌሎች ቃላት የመተካት ልማድ አለ። “ሙያዊ ሥልጠና” እና “ማኅበራዊ አገልግሎቶች” የሚሰጡባቸውን ተቋማት የሚያመለክቱትን “ወኅኒ ቤት” ወይም “ማረሚያ ቤት” የሚሉ ቃላት መጠቀም ይቀለናል። እንዲያውም “እስረኛ” ከሚለው ስብዕናን የሚገፍ ቃል ይልቅ “የሕግ ታራሚ” የሚለውን መጠሪያ እንመርጣለን። ይሁን እንጂ ከዚህ ሽፋን በስተጀርባ ስትመለከት ወንጀለኞችን ከብረት አጥሮች ጀርባ ለማኖር የሚወጣው ወጪ በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ መምጣቱና ወንጀለኞች በሚታሰሩበት ዓላማና እየታየ ባለው ውጤት መካከል ያለው ልዩነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መምጣቱ እስር ቤቶችን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተታቸው ትገነዘባለህ።

አንዳንድ ሰዎች እስር ቤቶች የታለመውን ዓላማ ማሳካት መቻላቸውን ይጠራጠራሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ የእስረኞች ቁጥር ከስምንት ሚልዮን በላይ የደረሰ ቢሆንም በብዙ አገሮች ውስጥ የሚፈጸመው ወንጀል በጎላ ሁኔታ እንዳልቀነሰ ይናገራሉ። ከዚህም በተጨማሪ በርካታ እስረኞች እስር ቤት የገቡት ሕገ ወጥ ከሆኑ አደገኛ ዕፆች ጋር በተያያዘ ወንጀል ቢሆንም የእነዚህ ዕፆች በየጉራንጉሩ መገኘት አሁንም ድረስ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ነው።

ያም ሆነ ይህ ብዙዎች እስራት የተሻለ መቀጮ ነው የሚል እምነት አላቸው። ወንጀለኛው ሲታሰር ፍትሐዊ እርምጃ እንደተወሰደ ይሰማቸዋል። አንዲት ጋዜጠኛ ወንጀለኞችን ከብረት አጥር ጀርባ ለማስገባት ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት “ወኅኒ ቤት የመወርወር አባዜ” ሲሉ ገልጸውታል።

ሕግ ተላላፊዎች እስር ቤት የሚገቡባቸው አራት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ:- (1) ወንጀለኞቹን ለመቅጣት፣ (2) ኅብረተሰቡን ለመጠበቅ፣ (3) ተጨማሪ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከልና (4) ወንጀለኞች ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ሕግ አክባሪዎችና ምርታማ ዜጎች እንዲሆኑ በማስተማር ለውጥ እንዲያደርጉ ለመርዳት ነው። እስር ቤቶች እነዚህን ዓላማዎች እያከናወኑ መሆን አለመሆኑን እስቲ እንመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ