የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 5/07 ገጽ 3
  • የብልጽግና ዘመን—ለእነማን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የብልጽግና ዘመን—ለእነማን?
  • ንቁ!—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2013
  • በበለጸገ ዓለም ውስጥ ድሆች የበዙት ለምንድን ነው?
    ንቁ!—2007
  • አንድ ቢሊዮን ሰዎችን ለመመገብ የሚደረግ ሙከራ
    ንቁ!—2005
  • ድሆች ይበልጥ እየደኸዩ ናቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2007
g 5/07 ገጽ 3

የብልጽግና ዘመን—ለእነማን?

‘የምንኖረው በበለጸገ ዓለም ውስጥ ነው’ ቢባል ይህን ሐሳብ ለመቀበል ይከብድሃል? አንዳንድ የበለጸጉ አገሮች ተዝቆ የማያልቅ ሀብት አላቸው። በ2005፣ የዓለም አጠቃላይ ብሔራዊ ምርት ከ60 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሆነ ተገምቷል። ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ ለሚገኘው ሕዝብ ሁሉ ቢከፋፈል ለእያንዳንዱ ሰው 9,000 የአሜሪካ ዶላር ይደርሰዋል። ይህ አኃዝ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

ይሁን እንጂ በዓለም ላይ የሚታየው ብልጽግና ያስገኘው ውጤት ከሚጠበቀው በጣም የራቀ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ባወጣው አንድ ጽሑፍ ላይ እንደገለጸው፣ በዓለም ላይ በጣም ባለጸጋ የሆኑት ሦስት ሰዎች ያላቸው ሀብት ድሃ የሚባሉ 48 አገሮች ካላቸው አጠቃላይ አገራዊ ምርት ይበልጣል። ከዚህም በላይ የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እንደገለጸው 2.5 ቢሊዮን ሰዎች የዕለት ገቢያቸው በጣም አነስተኛ ነው። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የተመጣጠነ ምግብና ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አያገኙም።

በዩናይትድ ስቴትስ ያሉ የማኅበራዊ ኑሮ ጠበብት “ድህነት የሚያሰጋቸው” ብለው በሰየሟቸው ሰዎች ላይ ጥናት እያካሄዱ ነው። እነዚህ ሰዎች ድሃ የመሆን አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው። ምንም እንኳ ይህች አገር ከፍተኛ ሀብት ቢኖራትም ከ50 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ሕዝቧ ወደ ድህነት እያሽቆለቆለ ነው።

በዓለም ዙሪያ ባሉ ግምጃ ቤቶችና ባንኮች ውስጥ ይህ ነው የማይባል ገንዘብ ተከማችቶ እያለ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በድህነት የሚማቅቁት ለምንድን ነው? በርካታ ሰዎች እያደገ ከሚሄደው የዓለም ሀብት ለመጠቀም ያላቸው አጋጣሚ በጣም ውስን የሆነውስ ለምንድን ነው?

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

በዓለም ላይ እጅግ ባለጸጋ የሆኑት ሦስት ሰዎች፣ በጣም ድሃ ከሚባሉት 48 አገሮች የሚበልጥ ሀብት አላቸው

[በገጽ 2, 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በዚህ የጡብ ማምረቻ ውስጥ በጉልበት ሥራ ላይ የተሰማሩት እነዚህ ልጆች በቀን ወደ 4.50 የኢትዮጵያ ብር ገደማ ይከፈላቸዋል

[ምንጭ]

© Fernando Moleres/ Panos Pictures

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© Giacomo Pirozzi/Panos Pictures

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ