የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 3/08 ገጽ 26
  • የአንዳንድ ነፍሳት ዓይን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንዳንድ ነፍሳት ዓይን
  • ንቁ!—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ዓይን ስለ ዓይን” ሲባል ምን ማለት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ስለ ዓይን የተሰጠ ጥበብ ያዘለ ምክር
    ንቁ!—2012
  • አስገራሚው የሦስት አፅቄዎች ዓለም
    ንቁ!—2000
  • ጤናማ ዓይን ይኑራችሁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
ንቁ!—2008
g 3/08 ገጽ 26

ንድፍ አውጪ አለው?

የአንዳንድ ነፍሳት ዓይን

◼ “ያለ አንዳች መዛነፍ የተደረደሩ በርካታ ሌንሶች።” የበርካታ ነፍሳትን ዓይን አስመልክተው ይህን የተናገሩት በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሉክ ሊ ናቸው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ:- እንደ ንብና ተርብ ያሉ የአንዳንድ ነፍሳት ዓይን ወደ ተለያየ አቅጣጫ ማየት የሚችሉ በርካታ ሌንሶችን ያቀፈ ነው። እያንዳንዱ ሌንስ የሚፈጥረው ምስል አንድ ላይ ተዳምሮ ሰፋ ያለ እይታን ለመፍጠር የሚያስችል ሲሆን ይህም የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን በሚገባ ለመለየት ይረዳል።

የሳይንስ ሊቃውንት ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸውን እንቅስቃሴዎች ለይቶ ለማወቅ የሚያስችሉ መሣሪያዎችንና ወደ ተለያየ አቅጣጫ ማየት የሚችሉ ካሜራዎችን ለመሥራት የአንዳንድ ነፍሳትን ዓይን አሠራር ለመኮረጅ ምርምር በማድረግ ላይ ናቸው። እነዚህ መሣሪያዎችና ካሜራዎች የተለያዩ ጥቅሞች ይኖራቸዋል። አንደኛው ጥቅም ከሕክምና ጋር የተያያዘ ነው፤ ለምሳሌ ያህል፣ ጨጓራ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመመርመር ያስችላሉ። የሳይንስ ሊቃውንት ሊሠሩት ያሰቡት ይህ የሕክምና መሣሪያ “ትንሹ ዘዴ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በሕክምናው ወቅት ታካሚው እንዲውጠው ይደረጋል። መሣሪያው ጨጓራ ውስጥ ከገባ በኋላ በዓይኑ አማካኝነት መረጃዎችን ይሰበስብና ያለ ምንም ገመድ እርዳታ መረጃውን ያስተላልፋል።

በተፈጥሮ ላይ የሚንጸባረቁትን ንድፎች አስመስሎ የሚሠራ አንድ የመሃንዲሶች ቡድን ከ8,500 በላይ ሌንሶች ያሉት ሰው ሠራሽ የነፍሳት ዓይን መሥራት ችሏል፤ የዚህ ዓይን መጠን ከስፒል አናት ያነሰ ነው። ይሁን እንጂ ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት ከነፍሳቱ ዓይን ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ ተርብ በአንዱ ዓይኑ ውስጥ ብቻ ወደ 30,000 ገደማ የሚጠጉ ሌንሶች ይገኛሉ!

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ:- ‘የተለያዩ ገጽታዎች ያሉት የነፍሳት ዓይን የተገኘው በአጋጣሚ ነው ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?’

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የንብ ዓይን የተወሰነ ክፍል ጎላ ተደርጎ ሲታይ

[በገጽ 26 ላይ የሚገኙ የሥዕል ምንጮች]

ከበስተጀርባ ያለው ፎቶ:- © Stephen Dalton/Photo Researchers, Inc. ጎልቶ የሚታየው ዓይን:- © Raul Gonzalez Perez/Photo Researchers, Inc.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ