የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/09 ገጽ 27
  • ውኃ የማያስገባው የሎተስ ቅጠል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውኃ የማያስገባው የሎተስ ቅጠል
  • ንቁ!—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2009
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2001
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • አደገኛ—ነፍሰ ገዳይ ተክሎች!
    ንቁ!—2004
ንቁ!—2009
g 4/09 ገጽ 27

ንድፍ አውጪ አለው?

ውኃ የማያስገባው የሎተስ ቅጠል

◼ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያጸዱ የፕላስቲክ ኩባያዎች፣ ዝናብ ቢዘንብባቸውም የማይረጥቡ መስኮቶች፣ እርስ በርስ ሳይፋተጉ የሚሠሩ ጥቃቅን ማሽኖች። የሎተስ ቅጠልን ሚስጥር ማወቅ ብንችል ኖሮ ከምናገኛቸው ጥቅሞች መካከል ከላይ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ ብቻ እንደሆኑ የሳይንስ ሊቃውንት ይናገራሉ።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የሎተስ ቅጠል የላይኛው ክፍል በዓይን ሊታዩ በማይችሉ ጉብታዎች የተሞላ ሲሆን እነዚህ ጉብታዎች ደግሞ ቅባትነት ባለው ነገር የተሸፈኑ ናቸው። እንደ ውኃ መከላከያ ሆነው የሚያገለግሉት እነዚህ ጉብታዎች በቅጠሉ ላይ የሚያርፉትን የውኃ ጠብታዎች ወደ ውስጥ ሰርገው እንዳይገቡ ያግዷቸዋል። ቅጠሉ ጋደል ያለ መሆኑ ውኃው የቅጠሉን ገላ ሳይነካ ኮለል ብሎ እንዲወርድ ያደርገዋል። ከዚህ የተነሳ የሎተስ ቅጠል ምንጊዜም የማይረጥብ ሲሆን በላዩ ላይ ያሉት ቆሻሻዎችና አቧራ በውኃ ነጠብጣቦቹ ታጥበው ስለሚወሰዱ ቅጠሉ ሁልጊዜ ንጹሕ ነው።

የሳይንስ ሊቃውንት እንደ ሎተስ ቅጠል ሁሉ ውኃ ወደ ውስጥ እንዳይሰርግ የማገድ ባሕርይ ያላቸው ነገሮች ለመሥራት ይፈልጋሉ። በውኃ ምክንያት ሊበላሹ የሚችሉ ጥቃቅን የሆኑ ማሽኖችም እንኳ ሳይቀር የሎተስን ቅጠል የሚመስል አሠራር ቢኖራቸው ጠቃሚ ነበር። “[የሎተስን ቅጠል አፈጣጠር በመኮረጅ] ሊገኙ የሚችሉት ጥቅሞች ቁጥር ሥፍር የላቸውም” በማለት ሳይንስ ዴይሊ ዘግቧል።

ምን ይመስልሃል? የሎተስ ቅጠል በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ